Wednesday, June 26, 2013

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት

rodas-teklu
ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሮዳስ ተክሉ እዚህ አትላንታ ከተማ በዋለው የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርባ ጉዳይዋ ሲታይ ከቆየ በኋላ ባለፍው ሰኞ MAY 20/2013 ….. 25 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሮዳስ ተክሉ ይህ የተፈረደባት የሰው ነፍስ በማጥፋቷ ወንጀሉንም መፈጸሟን በማመኗ ነው።
የኋላ ታሪኩ እንዲህ ነው። ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2009 አመሻሽ ላይ በአትላንታ የተፈጸመው ወንጀል መላው የአትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቅርብ፣ ነገሩን የሰሙና በሌሎች ከተሞች ያሉትን ደግሞ በሩቅ ያስደነገጠ ነበር። 3754 ቢፈርድ ሃይዌይ የሚባለው የአትላንታ መንገድ ላይ የጸጉር መከርከሚያ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ላይ የነበረው ኤርሚያስ አወቀ ፣ ማምሻውን ጭምር አምሽቶ እየሰራ ነበር። ከምሽቱ 8 ፒ ኤም አካባቢ ሮዳስ ተክሉ ሱቁ ድረስ መጣች።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሮዳስ ሱቁ ድረስ ከመጣች በኋላ ጭቅጭቅ ተጀመረ። እሱ እንድትወጣለት ቢጠይቃትም አልወጣችም። ይልቁኑ በእጇ ሽጉጥ ይዛ ስለነበር ፣ ስልኩን አንስቶ 911 ደወለ፣ ስልኩን ላነሳችው ኦፕሬተር “አንዲት ሴት ሱቄ ድረስ መጥታ ልትገለኝ እያስፈራራችኝ ነው፣ መሳሪያ ይዛለች .. እያለ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ ስልኩ ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የጥይት ድምጽ መስማታቸውን ይናገራሉ።
ፖሊስ ካለበት፣ ነገሩን የሰሙም በጸጉር ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ኤርሚያስ በደም ተነክሮ ወድቋል፣ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፣ ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አለፈ። በወቅቱ አንዲት ሴት ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ አይተናል ከሚል ጥቆማ ውጪ ማን ገደለው የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆነ።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 6 ግን ፖሊስ ሮዳስ ተክሉ የተባለችና የቀድሞ ፍቅረኛው ነች የተባለች ሴት በጥርጣሬ መያዙን አስታወቀ። እሷም ወደ እስር ቤት ተወሰደች። ኤርሚያስም የፖሊስ ምርመራ ከታወቀና ዶክተሮች የሞቱን መንስኤ ካስታወቁ በኋላ ፌብሩዋሪ 11 ቀን በርካታ የአትላንታ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጸጉር ቤቱ ደጃፍ የሻማ ማብራት ሰነ ስር ዓት ተካሄደ፣ በማግስቱ ፌብሩዋሪ 12 ጸሎተ ፍትሃት ከተደረገለት በኋላ አገር ቤት ተወስዶ እንዲቀበር በተያዘለት ፕሮግራም ይሄዳል ሲባል ፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገኛል በማለቱ እስከ ፌብሩዋሪ 24 ሳይላክ ቆየ። ፌብሩዋሪ 24 ቀን ግን አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ለቀብር ተላከ።
ከዚያ በኋላ ዜናው በአድማስ ሬዲዮም ሆነ አትላንታ ባለው ድንቅ መጽሔት ከወጣ በኋላ በወቅቱ የወጣት ሮዳስ ተክሉ ቤተሰቦች “እሷ በግድያው የለችበትም፣ ይህንን ድርጊት እሷ ትፈጽማለች ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሆነም ቀረ ላለፉት አራት ዓመታት ነገሩ ከፍርድ ቤት እስር ቤት ፣ ከ እስር ቤት ፍርድ ቤት ሲንከባለል ቆየ፣ የ ኤርሚያስ አወቀ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ላቀው ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጹት በመካከል ተጠርጣሪዋ ልጅ፣ በጠበቆቿ አማካኝነት “አእምሮዋ ትክክል አይደለምና ለፍርድ ልትቀርብ አይገባም” ብለው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ዳኞቹም የ አ ዕምሮዋ ነገር በሃኪሞች እንዲታይ ፈቅደው ቆይተዋል። በኋላ ግን ችሎት መቆም እንደምትችል በመታመኑ ፣ ጉዳዩ በከሳሽ አቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ሮዳስ ተክሉ ጠበቆች መካከል ክርክሩ ቀጥሎ አራት ዓመት ከፈጀ። እንደ አቶ ላቀው ገለጻ ፣ በመጨረሻ ላይ ሮዳስ ወንጀሉን መፈጸሟን እንድታምን ተጠይቃ “አዎ ፈጽሜያለሁ፣ ነገር ግን በደም ፍላትና ሳላስበው ያደረኩት ነው” ስትል በማመኗ ዳኛዋ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርደውባታል። ምናልባት ጥፋቷን ባታምን እና ነገሩ በክርክሩ ብትሸነፍ የሞት ፍርድ ሊጠብቃት ይችልም ነበር ብለዋል።
ዳኛዋ በፍርድ ውሳኔያቸው እንደገለጹት “ ኤርሚያስ ገበየሁን በ 10 ጥይት መግደል ሳይታሰብ፣ ባጋጣሚ የተደረገ አይደለም” ሲሉ ውሳኔያቸውን አጽንተዋል።
በተያያዘ ሁኔታ ሮዳስ ተክሉ እዚያው እስር ቤት እያለች አንዲት ሴት ልጅ መውለዷም ታውቋል። የወለደችው ግሬዲ ሆስፒታል በፖሊስ ታጅባ ሄዳ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ህጻኗን አንዲት ነርስ እዚያው ግሬዲ እያሳደገቻት መሆኑ ሲታወቅ፣ የህጻኗን አባት በተመለከተ ዳኛዋ “የቀረበልኝ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ስለሌለ፣ በልጅቷ አባት ጉዳይ የምሰጠው አስተያየት የለም” ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። 
(ምንጭ አድማስ ሬዲዮ አትላንታ)zehabesha.com
posted by Girum K.

ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ተጠየቁ

ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ተጠየቁ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ዛሬ በሚጀምሩት የሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካና ታንዛኒያ ጉብኝት በችግር ተዘፍቀው የሚገኙትን የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሀንንና የሰአብአዊ መብቶች ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል።

በአፍሪካ መገናኛ ብዙሀንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሚያደርጉባቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋልና ታንዛኒያ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ እና በፕሬስ ነጻነት ዙሪያ የተሻለ ሁኔታ ቢኖርም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ በመሆኑ ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ትኩረት እንዲሰጡ ድርጅቱ ጠይቋል።

የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ዳንኤል በቀለ ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰቡ አባላት ለሚያሳዩት ጥንካሬ እውቅና መስጠት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በርካታ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግን በመጠቀም 11 ጋዜጠኞችን መክሰሷን አመለክቷል።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት አፍሪካ የሰራቻቸውን ስራዎች ማጉላት ብቻ ሳይሆን፣ የሰብአዊ መብቶችን ማክበር ለአፍሪካ ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገር አለባቸው በማለት አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ሲጎበኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው። በማደግ ላይ ያለችው ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ያላት ቦታ እየተጠናከረ መምጣት ለፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ምክንያት መሆኑን አንዳንድ የፖለቲካ ምሁራን ይገልጻሉ።

ፕሬዚዳንቱ የሚጎበኙዋቸው ሶስቱ አገራት በአፍሪካ የተሻለ ዲሞክራሲን መገንባታቸው ይነገርላቸዋል።



























“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣    በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት  የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡  መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡DSCN0929




ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር  አሰሩኝ   ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር እዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ  እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኩዋ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝተዋል ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላር ሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡
በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ…ባካችሁ ተውኝ… ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች ፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር ?DSCN0916
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጠቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
DSCN0917ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም  ኢሜሌ ላይ የስኮላር ሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ  ነው  እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል ፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል እሱም ሪኮመንድ  አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ….(ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው  ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን  መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡  ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡

ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም ፡፡ ስትደበደብ፣ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ?  እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነውየነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
postd by Girum K.

Tuesday, June 25, 2013

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  -
እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።
የአይን እማኞች ” አካባቢው 24 ሰአት ሙሉ በስለላ ካሜራዎች የሚጠበቅ በመሆኑ ድርጊቱ በቤተመንግስት ጠባቂዎች ካልተፈጸመ በስተቀር በሌሎች ዜጎች ተፈጽሟል ብሎ  ለማመን አስቸጋሪ ነው” ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚኒሊክ ሆስፒታልንና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ላለፉት 5 ቀናት በተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም የሚኒሊክ ሆስፒታል ዛሬ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የህዝብ ግንኙነት እና የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ስልኮች አይነሱም። ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ውጤቱን በተመለከተ መውሰድ የሚችለው ፖሊስ በመሆኑ ፖሊስን መጠየቅ አለባችሁ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ የሚያውቁ አንድ ሰው እንደገለጹት አስከሬኑ በተገኘበት አካባቢ፣  በምሽት  ሰዎች እንደሚይዘዋወሩ ገልጸው ግድያው የተፈጸመው ምናልባትም በጠባቂዎች ሊሆን ይችላል ብለዋል። ያም ካልሆነ ግን መንግስት በመገናኛ ብዙሀን መረጃውን ይፋ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል ግለሰቡ ።
posted by Girum K,

በ 2005 ዓም ኢትዮጵያ ከወደቁ አገራት ምድብ ተመደበች

576820_643438789017118_1777115518_n
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት በእያመቱ በሚያወጣው የወደቁ አገራት ሪፖርት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር ፌልድ ስቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያ እንደ አለፉት አመታት ሁሉ ዘንድሮው የወደቁ ወይም በመውደቅ ላይ ካሉ 20 አገራት መካከል አንዷ ሆና ተመድባለች። የህዝብ ቁጥር ፣ የስደተኛ ቁጥር፣ የህዝብ ብሶት፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ያልተመጣጠነ እድገት፣ የመንግስት ህጋዊነት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የደህንነት ጥበቃ፣ የሊህቃን መከፋፈልና የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚሉት መስፈርቶች ተገምግዋል።
በዚህም መሰረት ከ1 እስከ 20 ያሉት አገራት ህልውናቸው አስተማማኝ ያልሆነ ከፍተኛ ችግር ያለባቸው ተብለው ተመድበዋል። ሶማሊያ ቀዳሚ የወደቀች አገር ስትባል፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቻድ፣ የመን፣ አፍጋኒስታን፣ ሀይቲ ፣ ሴንትራል አፍሪካ ፣ ዝምባብዌ፣ ኢራቅ ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ፓኪስታን፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኬንያ፣ ኒጀር፣ ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ተከታታዮችን ደረጃዎች ይዘዋል።
ከሀያዎቹ አገራት የተሻሉ ተብለው በሁለተኛው ምድብ ውስጥ ከሚገኙት መካከል ደግሞ ሶሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ኤርትራ፣ ማይናማር፣ ካሜሩን፣ ስሪ ላንካ፣ ባንግሊያዲሽ፣ ኔፓል፣ ሞሪታኒያ፣ ኢስት ቲሞር፣ ሴራ ሊዮን፣ ግብጽ ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኮንጎ፣ ኢራን፣ ማሊ፣ ርዋንዳ እና ማላዊ ተመድበዋል።
የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ በተሻለ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ጥንካሬ ላይ እንደምትገኝ በተደጋጋሚ ሲናገር ይሰማል። ይሁን እንጅ የፎሬን ፖሊስ መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ አመታት ይህ ነው የሚባል የደረጃ መሻሻል አልታየባትም። በዚህ አመትም ኤርትራ በአንጻራዊ መልኩ ከኢትዮጵያ በተሻለ ደህንነት ላይ እንደምትገኝ ሪፖርቱ ሲያሳይ፣ ኬንያ፣ ናይጀሪያና ሱዳን ደግሞ ከኢትዮጵያ አንሰው ተገኝተዋል።
posted  by Girum K.

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

ethio maids



በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በሪያድ “ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች” የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ
ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት  እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር  ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት  የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።
ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ ከቆየች በኋላ በስራ ብዛት እግሯን ስላመማት ከስራ መፈናቀሏንና ወደ ጅዳ ቆንሰል መጠለያ መጠጋቷን ገልጸውልኛል። ያም ሆኖ በመጠለያው ትኖር የነበረች ይህችው እና የአእምሮ ሁከት ይስተዋልባት ያልነበረው እህት ባልታወቀ ምክንያት ሊነጋጋ ሲል ከቆንስሉ ግቢ በር ታንቃ መገኘቷን እንዳስደነገጣቸው እማኞች በእንባ እየታጠቡ አስረድተውኛል።
“መረጃ ለጋዜጠኛ ከሰጣችሁ ከመጠለያ ትባረራላችሁ!” የሚል ማስጠንቀቂያ ከመጠለያ ሃላፊዎች የተሰጣቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እኒሁ የአይን እማኝ ተፈናቃዮች “ታመው የሚሰቃዩት እና እያበዱ የሚመጡት አህቶች ሁከትና ረብሻ የቀረነውን ሊያሳብደን ነው” ሲሉ ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ገልጸውልኛል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሟች ማንነትና ተዛማጅ መረጃዎችን ለማሰባስብ ባደረግኩት ሙከራ ሟች ከመሞቷ ከአስር ቀን በፊት ከቆንሰሉ በመጠለያ ስትጨናነተቅ ያገኟት አንድ ኢትዮጵያዊ በጉዳዩ ተቆጭተው በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ያነሱትን ምስል አግኝቼ ተመልክቸዋለሁ።  በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምሰል ቪዲዮ ላይ ሟች የመጣችው ከወሎ ሃይቅ አካባቢ መሆኑን ያስረዳች ሲሆን አንድ አመት ከሰባት ወር የሰራችበትን ደመወዝ አረቦች ሰጥተው ከመጠለያው ቢጥሏትም ገንዘቧ የት እንደ ገባ እንደማታውቅ በትካዜ ስትገልጽ ትታያለች። የምትፈልጊው ምንድን ነው ብለው ሲጠይቋትም ወደ ሃገሯን ለመግባት ብትፈልግም ሊሳካላት አለመቻሉን ተስፋ ቆርጣ ስታስረዳ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ  ምስል ያሳያል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከበርካታ ወራት በፊት አንድ ወንድም ወደ ቆንሰሉ ግቢ እንዳይገባ ተከልከሎ በቆየበት በር ህይወቱ ማለፉ አይዘነጋም ። አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በቆንስሉ ግቢ አትገቢም ተብላ በመታገዷ ራሷን ስታ እንደነበር ይታወሳል። ይህችው እህት ከቆንሰሉ አካባቢ በሚገኝ ዛፍ ተንጠልጥላ ሶስት ቀናት ከቆየች በኋላ ያለቸበት ሁኔታ ታውቆ ከዛፉ እንድትወርድ ሲያግባቧት አሻፈረኝ በማለት ራሷን ከዛፉ ወደ መሬት ወርውራ መግደሏ ራሷን አጥፍታለች።
ከሳምንት በፊት ታዋቂው የሳውዲ እለታዊ ጋዜጣ ሳውዲ ጋዜጥ ተቡክ ተብሎ በሚታወቀው የሳውዲ ግዛት አንድ ኢትዮጵያዊት ራሷን መግደሏን ማስታወቁን በቁጥር 2 ዝንቅ መረጃየ ላይ ዘግቤው ነበር። በተመሳሳይ ዜና በዚያው ከሳምንት ካሚስ ምሽት ተብሎ በሚታወቅ አንድ የሳውዲ ግዛት አንዲት እህት “ራሷን ገድላለች” ተብሎ ሬሳዋን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑንም መረጃውን አቀብየ እንደነበር አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋና ከተማዋ በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት የ26 አመት ወጣት የኮንትራት ሰራተኛ “በአሰሪዎቿ ደረሰብኝ የምትለውን አስከፊ እንግልት ለመበቀል የ6 አመት የአስሪዎቿን ሴት ህጻን መግደሏን አምናለች” የሚል አንገት ሰባሪ ዜና የተሰማው ትናንት ሲሆን ዛሬ የወጡት የሳውዲ ጋዜጦችም መረጃውን ይፋ አድረገዋል።
በኮንትራት ሰራተኞች ዙሪያ ሊሰሙት የሚዘገንን መረጃ መተላለፍ ከጀመረ አመታት የተቆጠረ ቢሆን መንግስት ትኩረት ስላልሰጠበት ችግሩ ሲባባስ ቆይቷል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን በስደቱ እየሆነ ላለው በሚመለከት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ዘጋቢ ፊልም ከታየ ወዲህ መንግስት ጉዳዩን ለመቆጣጠር ቁርጠኛ አቋም እንደሚወስድ ቃል መገባቱ አይዘነጋም።
ከኮንትራት ስራ ጋር በተያያዘ በሳውዲ አረቢያና ኢትዮጵያ መካከል የኮንትራት ሰራተኛን በሚመለከት የሁለትዮሽ ስምምነት እንደሌለ የጅዳው ቆንስል አቶ ዘነበ ከበደ በጀርመን ራዲዮ “እንወያይ” ፕሮግራም ተጋብዘው ባደረጉት ውይይት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ከሶስት አመት በፊት በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 120 ሺህ ገደማ ይገመት የነበረ ሲሆን የኮንትራት ሰራተኞች ያለ ሁለትዮሽ ሰምምነት መምጣት ከጀመሩበት ካሳለፍነው ሶስት አመት ወዲህ የኢትዮጵያውያኑ ቁጥር 500 ሺህ መድረሱ ይገመታል።
(ነቢዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ “ከዝንቅ መረጃ” አምዱ ካቀረበው የተወሰደ)
እንህ ሰው አቶ ሃጎስ ይባላሉ እናማ አቶ ሃጎስ እስራኤል ከተማ በተደረገው ስብስባ ላይ በመገኝት ጥያቄ እንዳላቸው በማሰታውቀ እንዲህ በማለት ለአቶ ኦባንግ ሜቶ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል::

አመሰግናለሁ እድል ለተስጠኝ እ..... ሃጎስ እባላለሁ የመጣሁትም እየሩሳሌም ነው :: አንድ ሶስት አራት ጥያቄዋች አሉኝ፣ ጥያቄዎች እንደምትመልሱልኝ በልብ አመስግናለሁ እንድምትመልሱልኝም ተስፋ አለኝ ::

የመጀመሪያው ጥያቄ ...እዚህ ላይ የምትናገሩት ወይም በፊልም የሚታየው ጉዳይ የ19 ወይም በደርግ ግዜ ወይም በሐይለስላሴ ግዜ የሚደረገው የነበረውን ሁኔታ ነው የምታሳዩት :: (ጥያቄ ነው)
ምናልባት እነዚህ ጉዳዮች እንዴት ልታዩት ትችላላቹ ?ዕውን ነው የሚሰራውና ፣ ሰው ነው የሰራው ይህን ነገር አቀናብራችሁ ለመምጣት ሕብረተሰቡን ለማሳመን ይህን የምታመጡት ምን ይሀል ሕዝብስ ተቀባይነት...... በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ሄዳችሁ እንዴት ተቀባይነት ሊያገኛ ይችላል ?

በሁለተኛው ጥያቄ ንብድነው ...ምናልባት ተቃዋሚ አለ የመንግስት ወገን አለ:: ከውጪ ሆኖ የፕለቲካ መንዛት ሳይሆን በጠረቤዛ ላይ ተገናኝታቹ ተወያይታቹ ችግሩን የማትፈቱት? እኔ የማንኛውም ደጋፊ አይደለሁም:: ይሄ በጠረቤዛ ውይይት የሚፈታበት መንገድ ለምን አትፈጥሩም ? የኢትዮጵያም መንግስትም ይሁን በተቋሚው ይሁን ? በተለይ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ማንኛውም ተቋዋሚው ሐይል ገብቶ በጠረቤዛ ተወያይቶ ሰለ ልማት ሰለሀገር እናድን እያለ ነው መንግስት ይሄንን ለምን አትገቡም ?

ሰውየው ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ ነው የመጡት ተብለዋል ተጠይቀዋል ፣ ማለት መግለጫ ሰተዋል :: ይሄ ሰውየ በጋምቤላ አካባቢ በአንዋክና በሌሎች ብሔረሰቦች በጭፍጨፋ.... በወንጀል የሚፈለግ ነውና ይሄንን ምን ይሀል ታማኝነትን አለው ወይስ ትክክል ነው ወይስ አይደለም እንዴት ነበር ? የሚል ከሳቸው መልስ እፈልጋለሁ :: ብለው ማልሳቸውን ከአቶ ኦባንግ ለመስማት ቁጭ አሉ::

ወይ አቶ ሃጎስ

የአቶን ኦባንግ መልስ እንደሚከተለው ነበር

አመሰግናለሁ ወንድሜ ሃጎስ ... ምን መሰለህ አንድ ያልገባሕ ነገር አለ ::ሀገራችን በአሁኑ ሰአት አንድ ሰው ኢሐደግን የሚቃወም ሰው እንዲህ አይነት ጥያቄ መጠየቅ አይችልም :: አሁን እኛ ያለነው ሌሎች ሰዎች ሀገር ነው :: አንተ የልብህን እንደዚህ መነጋገር ትችላልህ ::አንተ የጠየከው ጥያቄዎች በሙሉ መለሲ መቶ በመቶ መልሱ አንተ ውስጥ ላይ ::ምንም ጥያቄ የለህም:: አንተ ያደክ ሰው ነው ፣ ክፉና እውነተኛ መሆኑን ታውቃለህ ::አንተ የጠየከው ጥያቄዎች፣ ስለቪዲዮ በእውነት በቃ የሰው ልጅ አይምሮ ብንመራመር ብንችል ኖሮ እዚጋ ያሉት በሙሉ... እሱም እራሱ ትክክለኛ መልስም አንተ ጋር መሆኑን እናውቅ ነበር ግን አንችልም ::

በዚሕ ላይ አንድ ነጋር ብቻ አሁን ለምሳሌ በጋምቤላ ያልከው፣ ቅድን ብያለሁ አንተ የምትናገረው የኢሐደግ ቋንቋ ነው ::ግዜው አልፏል አሁን አይሰራም ::እውነቴን እኮ ነው ከልቤ ነው የምናገረው፣ ግን አንድ ነገር ፣ አንድ በጣን እውነት ነገር የጠቀስከው ነገር አለ::ለዛውም ነገር በወንድምነትም በእውነት እኔ ውስጥም ምንም ጥላቻ የለም አንተ ወንድሜ ነህ እወድሀለሁ፣ ኢትዮጵያዊ ስለሆንክም ወንድሜ ነህ:: አገራችን ያለ ክፉ ነገር ለመሰተካከል አንተ እንዳልከው መነጋገር ያስፈልጋል ::

ይሄ ነው አሁንም ይሄ ቪዲዮ ወሸት ነው ወይ ? ጋምቤላ እያለህ ጨፈጨፈ ...እኔ እኮ እኛ ቀርተን መለስም እራሱ 424 ሰዎች ሲጨፈጭፍ፣ መለስ እራሱ ነገረን.. ሶስት ወታደሮች ናቸው እነዚህን ሰዎች የገደሉት:: እኔ አይደላሁም መለስ ነው:የጎሳ አይደለም :: እኔ የማነጣጥረው ምን ላይ እንደሆነ ታውቃለህ ? ያው አንተ ያልከው የጠቀስከው ነገር አለ፣ ለምንድነው ሀገር ቤት ያለው አንድ ላይ መነጋገር በተለይ ተቋዋሚዎችና ኢሐደጎቹ የመነጋገር ግዜው ብዙ አጋጣሚው ነበር ::ያም እልፏል አሁንም ዝግጁ ነን ::ለመወያየት፣ ለመነጋገር፣ ችግሩን ለማፈታት ዝግጁ ነን :: የኢሕድግ መንግስት እንጂ ሰዎቹ በሙሉ ዝግጁ ነን ::

ላንተ የምነግርህ ምንድን ነው ፣ አሁን እዚህ ጋር ይሄን ነገር ማወቅ አለበት ወንድሜ ሀጎስ ኢሕድግ ያሚጠቀመው እኮ በትግሬ ስም ነው :: ትግሬዎቹ በህዝብ ብዛት በጣም ጥቂት ናቸው :: በቂ መሳሪያ የላቸውም ::ኢትዮጵያኖችን ለመግደል:: በቂ ጉልበት የላችውም ኢትዮጵያን እስከዘላለም ለመግዛት ::አንድ ሰው እኮ ከ10 ሰዎች መጣላት አይችልም :: አሁን ነገ ችግር ቢፈጠር፣ መለስ በትግሬ ስም የተሰራው ጥላቻ፣ ቤኔሻንጎል ሂድ ጋምቤላ ሂድ የትም ሂድ እሱ የሰራው ጥላቻ፣ እያንዳንዱ ሰው ያውቃል :: ነገ ይሄ መንግስት.... ማን ላይ ነው ጉዳቱ የሚፈጠረው ?ትግሬዎቹ ናቸው :: በአሁኑ ሰዓት፣ አንተን ቀርቶ እኛ የትግሬ ተወላጅ ያልሆኑ ሰዎች፣ ትግሬዎችን መጠበቅ አለብን :: we have to protect them because they are minority. ስልጣን ላይ እያሉ፣ መሳሪያ እያላቸው... ይሄን ነገር አስብበት ሀጎስ...አንድ ሰው ከአሰር ሰዎች አይጣማም:: 5ሚሊዮን ከ 90ሚሊዮን አይጣሉም::አሁን እኔን ቀርቶ ማንንም ኢትዮጵያዊ ....ኢትዮጵያ ወስጥ እኮ የተቀበረ ፈንጂ አለ፣ ያን ፈንጂ የቀበራው ማነው? መላስ ነው ::

ታውቃለህ የኛ ሰዎች ደግሞ በደምብ ያልተማሩ ሰዎች ናቸው :: አሁን ሰዎች ምን ይላሉ ? ልጄ ሞትዋል፣ የገደለውም የኢሕድግ መንግስት ሳይሆን ትግሬ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ :: ኡጋዴን አካባቢ ሂድ፣ ጋምቤላ አካባቢ ሂድ በትግሬ ሰም ብቻ፣ ነገ የሄ መንግስት ቢወድቅ ችግሩ የት እንደሚደርስ አንተ ታውቃለህ እኔም አውቃለሁ ::ለዚህ ነው ቅድም ያልኩት ያንተ እዚህ ጋር መምጣት በጣም ጥሩ ነው ::አሁን እውነተኛን ነገር መነጋገር አለብን :: የተውንኮል ፣ ያድብቅ አይሰራም የትም አያደርስም ::ጉዳቱ ታውቃለህ ርዋንዳ የተፈጠረውን ሰዎች ምን ይላሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ ይፈጠራል ይላሉ :: ይሄ ነገር እንዳፈጠር ፣እብዳንተ አይነት ከኛ መካከል መምጣት እራሱ በጣም አመሰግናለሁ በጣምም አከብራለሁ:: ምክንያቱም እንፈልግሀለን አሁን እሉ የኛ ወገን ትግሬዎቹ፣ በስልጣን በገንዘቡም በምኑም አይናቸውን የጨፈኑ አሉ :: ምን እየመጣ እንደሆን አያውቁም ::ነገ ችግር ቢፈጠር እንኝህ ናቸው ይላሉ ::ያን አንፈልገም :አዎ ምውነጋገር አለብን :: ታውቃለህ በደርግ ግዜ ወጣት ነበርኩኝ፣ መአት ትግሬዎች ጋምቤላ ተወሰደው ነበር ፣ስንት ልጆቻቸው በወባ የሞቱባቸው፣ መንግስቲ ሐ/ማ ነበር እዛ ያስቀመጣቸው ፣ ሆስፒታል ወዳለበት ያስቀምውጣቸው፣ አንድ አንድ ሰዎች .... እኔ ራሴ አውቃለሁ ትግሬ በመሆናቸው ብቻ ወንበዴ ይሉ ነበር :: ትግሬ በመሁናቸው ብቻ እንደዛ ባይሆኑም፣ ይሰማኝ ነበር፣ ሰውን ወንበዴ ማለት ትግሬ ሰለሆነ ::

መለስ ጫካ የገባበት ምክንያት ትግሬ ተበድሏል ብሎ ነው ፣ከጫካ ሲመለስ ፣ ጫካ የገባባትን ሆነ እንደውም የባሰ::Mels think he went to the bush because Mengistu Hayelmaryam made to go the bush .Mels made Obang to speak about whats going on in the country .My point is two wrong doesn't make right. The Tigra are our brothers. They made a mistake, someone made a mistake in there name off course, tomorrow they are minority we need to work to protect them . Because they are us . አሁንም የመለስ መንግሰት ወይም ኢሐድግ መንግሰት የሚሰራው እነሱና እኛ ፣ በኛ በኩል እኛና እነሱ የሚባል ነገር የለም አንድ ነን :: እና ይሄን ነገር ለመሰራት ቅድም እንደተናገርኩት ለአንተ አቶ ሀጎስ አገራችን ያለው እውነታኛ ምን እንደሆነ ታውቃለህ:: what we need now is አንተ እየሰራህ እዚህ መምጣትህ እራሱ ትልቅ ምስጋና ላንተ ነው :: ውሰጥ ምንም ጥላቻ የላም :: በአላማ አንስማማም :: ለአዲስቷ ኢትዮጵያ ለነገ ኢትዮጵያ ሁላችንም መነጋገር መወያየት በጣም አስፈላጊ ነው:: እና ቅድም እንደነገርኩህ ይህን መመላስ የለብኝም :: የጋምቤላን አንተ ታውቃለህ :: ማንንም አልገደልኩም፣ ሰዎች ያውቃሉ :: ቪዲዮ ያለው ዱሮ የሐይለስላሴ ጥቁርና ነጭ ቪዲዮ የለም :: አሁን ሁሉንም ታውቃለህ :: ይሄ ሀሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ የለው ነገር ሁሉም እውነት ነው ማልት ውሸት ነው:: ይሄን ሞኝ እንኳን ያውቃል ይሄን ነገር አንተም ማወቅ አለብህ :: በእውነት ኢትይዮጵያ ውስጥ specially ኢሓደግ የሰራው ሰራ በደል ለማሰተካከል በበሄራእኢ እርቅ ካልሁነ በስተቀር መአት ደም ይፈሳል :: ያ ደም እንዳይፈስ መነጋገር አለብን ::Denied it's not going to get us anywhere . We been denied for the last ...አንድ ወንድማችን ብልዋል ::you believe in the country one ethnic group , by been that ethnic group, you can get a job . ኢትዮጵያ ውስጥ እራሱ.... ይሄን ነገር እውነት መነጋገር አለብን ትግሬ በመሁንህ እራሱ you can get title.

አንድ ምሳሌ ልስጥህ፣ ከአውስትራልያ እንድ ሰው ሄደ አዲስ አበባ ሲደርስ፣ they wants him to pay ቀረጥ ሁለት ኮምፒተር ነበረው ፕሮጀክተር ነበረው እና 12ሺ ብር አሉት፣ ልጁ 12ሺ የለኝም አለ ፣ በቃ they said the will take the computer .እና እንድ ሰው ጠየቁ ሁለቱ የትግሬ ተወላጆች በትግርኛ ቋንቋ ይነጋገራሉ you know , where is he from ? ልጁ ትግርኛ ይችላል በትግርኛ መልስ መለሰ እሱ ያለው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ?" አባቴ ዘመዶቹ ጫካ ገቡ ፣ ጫካ የገቡት ሊታገሉ ነው :: ለዚህ አይደለም የታገሉት" :: በትግርኛ ብቻ ይሄንን ሰላለ፣ አዎ ለካስ አንተ የኛ ነህ በለው ቀረጥ የለም ለምን አልተነገረኝም አለ :: ተማልከት እንደዚህ አይነት ማንግስት፣ ያንን ቋንቋ በመናገርህ ብቻ ሀጎስ The problem in our country so deep we cannot ignore we cannot pretend . Pretending is not working It's not going to work .It will explode ,ዛሬ ላይሆን ይችላል ፣ ነገ ይሆናል :: ዞሮ ዞሮ እኛ ነን :: እውነተኛው ካለ አቶ ሀጎስ you know exactly what's the government is doing . በየትኛውም መንገድ አንድ ወታደር told me the video you were denying በብዛት ሱማሌን ለመዋጋት የተላኩት ወታደሮች የትግራይ ተወላጆች አልነበሩም :: ለምን ኢትዮጵያኖች አይደሉም? እሁን ቶርነት ቢፈጠር ሌላ ጎሳ ነው ከፊት የሚጋፈጠው ለአገሪእቷ ለመሞት :: ያን ያህል ጥሩ ናቸው ? ይሄን ነገር ለማሰተካከል እውነተኛ ትክክለኛ ውሰጣችን ያለ መሆን አለበት ::ኢሐደግ በጣም ትልቅ ጥፋት ሰርቷል ::ያጥፋቱ መለስ የሰራው ፣ለሌላ ጎሳ ቀርቶ ለራሱ ጎሳ ነው የሰራው :: መለስ ለራሱ የቆፈረው ጉድጓድ ትግሬዎቹ ወደ መውጫችን ይዘን እዛ ጉድጓድ እንዳንገባ ህኒና ያለው ሰዎችን መስራት አለንብን እያንዳንዳቸ :: እነዚህ ወብድሞቻችንን ለመጥለፍ we have to think big , we have to be honest .በሚቀጥለው አመት for people who are here, አገራችን ችግር በጥላቻ መፍታት አንችልም :: we cannot kill each others. We have die for so long we are dying in red see ,we are dying in prison, our woman been raped , we have suffer so much .ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተበደለ ጎሳ የለም :: በቃን በቃን :: እነዚህን ሰዎች who have done the wrong let us correct them .እንደ ሀጎስ እኛ መሀል መምጣቱ ፣ ሀጎስ እኮ የኛ ጠላት አይደለም :: የኛ ጠላት ትግሬ አይደለም ፣የኛ ጠላት አማራ አይደለም፣ ይኛ ጠላት ኦሮሞ አይደለም :: የኛ ጠላት ሲሰተሙ ነው ::ያ የኢሐደግ ሲስተም ነው ጠላቱ እንጂ ትግሬ አይደለም እና ሀጎስ የኛ ጠላት አይደለም ወንድማችን ነው ::


ምቼም ሀጎስ ይቺን ምክር ወሰዶ ሌሎቹን ከዘረኝነት ወደ ኢትዮጵያዊነት ይመልስበት ይሆን ? (ይቺን እኔ ነኝ የጨመርኩበት)