Monday, August 26, 2013

ኖርዌይ ኤምባሲ እና ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው Disagreement brewing between Engineer Hailu and Norway Embassy

Disagreement brewing between Engineer Hailu and Norway Embassy
Written by  ናፍቆት ዮሴፍ, AddisAdmassNews.com
“ያከራየኋቸውን ቤት ለመልቀቅ እምቢተኛ ስለሆኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቄያለሁ”
- ኢ/ር ኃይሉ
ኖርዌይ ኤምባሲ ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል የተከራየውን ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ለ15 አመታት ሲጠቀምበት እንደቆየ የገለፁት የአዲስ አድማስ ምንጮች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግብ የተፈጠረው ቤቱን ልቀቅ፣ አልለቅም በሚል ነው ብለዋል፡፡ በ97 ምርጫ የምርጫ ዘመቻ ቅንጅትን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ ከኤምባሲው ጋር በነበራቸው የኪራይ ውል መሰረት ከ7 ወራት በፊት ቤቱን እንዲያስረክባቸው እንደጠየቁ ተናግረዋል፡፡ በ3200 ካሬ ሜትር ግቢ ውስጥ የተሰራው ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ህንፃ በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፡፡ 
ቤቱን ስለምንፈልገው ልቀቁልን በማለት ከሰባት ወራት በፊት በደብዳቤ ብንጠይቅም፤ ኤምባሲው ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም የሚሉት ኢ/ር ሃይሉ፣ ከአንድ አመት በፊትም ኤምባሲው ቤቱን እለቃለሁ ቢልም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ብለዋል፡፡ “ቤቱን በትክክል ከፈለጋችሁት ግዙን” በማለት ለኤምባሲው አማራጭ አቅርበው ተቀባይነት እንዳላገኘም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 
ጉዳዩን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቃቸውን ኢ/ር ኃይሉ ጠቅሰው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ኤምባሲው ቤቱን እንዲለቅ ጥያቄ አስተላልፏል ብለዋል፡፡
“ህግና ስርዓትን ተከትዬ ቤቱን እንዲለቁ በትዕግስት ጠብቄያለሁ፡፡ እምቢ ካሉ በግል ንብረቴ ከእነርሱ ጋር እንካ ሰላንቲያ አልገጥምም” ያሉት ኢ/ሩ፤ ጥቁርን በመናቅና በማን አለብኝነት የሚካሄደውን ህገወጥነት ፈፅሞ አልቀበልም ብለዋል፡፡ ኤምባሲው የያዘብኝ ቤት ከመኖሪያ ቤቴ ጋር በአጥር ስለሚገናኝ በቤቴ በኩል አፍርሼ በመግባት ግቢውን ለማስተካከል ወስኛለሁ ብለዋል ኢ/ር ኃይሉ፡፡ ወደ ኤምባሲው በተደጋጋሚ ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ምክትል አምባሳደሯን ለማነጋገር ብንሞክርም “አሁን ቴሌ ኮንፈረንስ ላይ ነኝ፤ ማናገር አልችልም” የሚል ምላሽ በፀሀፊያቸው በኩል ተናግረው፤ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ 
ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ክፍል ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሀላፊ ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ለስብሰባ ከግቢ ውጭ ናቸው በሚል ምላሽ ልናናግራቸው አልቻልንም፡፡

Sodere news Amharic 

ትንሽ ስለ ‘መለሲ-ዝም’: ከኢህአዴጎች የምስማማበት ነጥብ .Abraha Desta


ሳስበው ሳስበው ስለ ‘መለሲዝም’ ሰበካ የተጀመረ ይመስለኛል። በመለስ ማመናቸው ችግር የለብኝም። ግን መለስ ፈጣሪያቸው መሆኑ እየነገሩን ነው። ብዙ ነገሮች በሱ ስም እየተሰየሙ ናቸው። እነሱ እንደሚነግሩን ከሆነ የኢህአዴግ ፖሊሲ የመለስ ነው፣ መለስ ወታደራዊ መሃንዲሳቸው ነበር፣ መለስ አንቀሳቃሽ ሞተራቸው ነበር፣ የኢህአዴግ ሓሳብና ተግባር የመነጨው ከመለስ ነበር፣ ባጠቃላይ መለስ ሁለመናቸው ነበር።

ለዚህም ነው የኢህአዴግ አባላት አውቀውም ሳያውቁም መለስ የተናገረውን እንደ ፓሮት የሚደግሙት። በራሳቸው ማየት ሳይችሉ መለስ በመራቸው ይጓዛሉ። ለዚህም ነው መለስ ያወጣውን ፖሊሲ መተግበር የማይችሉ። ፖሊሲው መተግበር ያልቻሉበት መንገድ ማየት ስለሚሳናቸው ፖሊሲው ጥሩ መሆኑ ተናዘው ችግሩ ያለው ግን አፈፃፀሙ ላይ መሆኑ ይለፍፋሉ።
ግን አንድ ትክክል ወይ ጥሩ የሆነ ፖሊሲ እንዴት ላይፈፀም ይችላል? ፖሊሲ’ኮ አፈፃፀም ነው። ፖሊሲ ከህልም የሚለይበት ዋነኛው መስፈርት ስለሚፈፀም ነው። ስለዚህ አንድ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ችግር ካጋጠመው ፖሊሲው ትክክል አይደለም ማለት ነው። ግን የመለስ ልጆች ‘ፖሊሲው ስህተት ነው’ ብለው የማጋለጥ ዓቅሙና ድፍረቱስ አላቸው? አይመስለኝም። ምክንያቱም ፖሊሲው የመለስ ነው። ፖሊሲው ስህተት እንደሆነ መናገር ማለት መለስ እንደሚሳሳት መመስከር ነው። መለስ ደግሞ ፈጣሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ከነ ስህተቱ ‘የመለስ ሌጋሲ ወይ ራእይ’ እያሉ የመለስን የተሳሳተ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማስቀጠል የሚባዝኑ።
ከኢህአዴግ አባላት የምስማማበት ነጥብ አለኝ፤ መለስ ሁለመናቸው ነው። እሱ የተናገረውን ያደርጋሉ፣ ይፈፅማሉ። ከነሱ ጋር የምስማማበት ነጥብ ይሄ ነው። ይሄንን ነጥብ ትርጓሜ እንስጠው።
የኢህአዴግ አባላት (እነሱ ራሳቸው እንደሚነግሩን) መለስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዕይታ ምንጫቸው ነው። አዎ! ነው። ይህ ማለት አባላቱ ምን መስራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው መለስ ይነግራቸው ነበር ማለት ነው። እነሱም ‘የታላቁ ባለራእይ መሪ’ ትእዛዞች ተቀብለው ይተገብሩ ነበር ማለት ነው።
የመለስና የአባላቱ ግንኙነት እንዲህ ከነበረ መለስ dictate ያደርጋቸው ነበር ማለት ነው። በእንግሊዝኛው አጠራር ሌሎችን dictate የሚያደርግ መሪ Dictator ይባላል። ስለዚህ ከተግባራዊ ትርጓሜው ተነስተን መለስን ስንገልፀው Dictator ነበር ማለት ነው። “Dictator’ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ‘አምባገነን’ (ብትግርኛ ‘ዉልቀ መላኺ’) የሚል ትርጓሜ ይይዛል። ስለዚህ ‘ሁሉም ወይም አብዛኞቹ የፓርቲው ስራዎች የመለስ ነበሩ’ በሚል ከተስማማን ‘መለስ አምባገነን ነበር’ በሚልም መስማማት ይኖርብናል።
እኔ ‘መለስ አምባገነን ነበር’ ሲል ‘የሁሉንም አድራጊ እሱ ነበር’ እያልኩኝ ነው። እናንተም በራሳቹሁ ሚድያና አንደበት ተመሳሳይ ነገር እየነገራችሁን ነው። ስለዚህ ሓሳባችን አንድ ነው። ተስማምተናል። በመለስ ስራና ስያሜ ላይ ልዩነት የለንም።
(ስለ መለስ ላለመፃፍ ዕቅድ የነበረኝ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ግን ስለሱ እያስታወሱ አስቸገሩኝ)

Saturday, August 24, 2013

ሰበር ዜና ...በ ማች መለስ ዜናዊ ሙት አመት ላይ አንድ ቄስ ነኝ ባይ ያደረጉትን ንግግር ቪዲዮ ይመልክቱ......እውነት ከ አንድ መንፈሳዊ አባት ይህ ይጠበቃል??????

አዲሱ አስተምህሮተ ክርስትና
በ1997 ምርጫ ሰሞን የሃይማኖት ሰዎች በቤተመንግስቱ አካባቢ ጥሪ ተደርጎላቸው ተሰብስበው እንደነበር ትዝ ይለኛል። ያንጊዜ ኦርቶዶክሳዊቷን ቤተክርስቲያን ወክለው ከተገኙት ውስጥ አንድ ሰው ተነስተው መለስ የሚባል ሰው አገር አንደሚገዛ በትግራይ የቀየ ንግርት አለ ብለው ተናግረው ነበር። ይህንን ተከትሎ አንድ የካቶሊክ ተወካይ ‘ አይ እነዲህ ያለነገር ልክ አይደለም ቤተመንግስት እጣን እጣን ቤተክርስቲያንም ፐለቲካ ፐለቲካ ስትሸት ደግ አይደለም እነዳሉ አስታውሳለሁ።
የባሰ አታምጣ አለ ያገሬ ሰው። ዛሬ ደግሞ ለቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ለመጽሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዋ የማይታዘዙ ‘’አባት’’ ለማየት በቃን። ‘’መነኩሴው’’ ከመጀመሪው የተሰጣቸውን ለ 2 ደቂቃ ብቻ ንግግር የማቅረብ ፈቃድ በራሳቸው ማን አለብኝነት ወደ አራት እንዳሳደጉት ነግረውናል። ለነገሩ አራት ብቻ ሳይሆን ከ 10-15 ደቂቃ ሳይናገሩ አልቀሩም። ‘’በነገር ብዛት ሃጢአት ሳይገባ አይቀርም ‘’ እንዲል መጽሃፍ ቅዱስ ሰውየው ንግግራቸውን ባስረዘሙ ቁጥርም መጽኃፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ደጋግመው ጥሰዋል። ገና ሲጀምሩ እውነት ማነው? ብለው ጠይቀው እራሳቸው መልስ ሲሰጡ ‘’ እውነት ክርስቶስ ነው’’ የሚለውን ቃል በመለወጥ ‘’ እውነት አቶ መለስ ነው’’ አሉን። ለጥቀውም ስለ አቶ መለስ ስራ ሲተርኩ ‘’ ቀድም ሲል አልታየም ወደፊትም እስከወዲያኛውም አይታይም’’ በማለት ጅማሬ እና ፍጻሜ የሌለውን እግዚአብሔርን በማመሳሰል  መለስን አልፋ ኦሜጋ አድረገዋቸዋል። በእግረመንገዳቸውም ቀድመው ክቡር ነገር የሰሩትን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አንኳሰው ወደፊትም ያሉትን ገዝ’ተዋል ማለት ነው። እኝህ ‘ሰባኪ’ ሃወሪያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ምእራፍ 2 ላይ ከጻፈው አና በክርስቶስ አንድ ስለመሆን ከተናገረውጋር አመሳስለው አቶ መለስን የክርስቶስ አቻ አድርገዋቸዋል። ይህንንም ሲያስረግጡ ‘’እዚህ ያለነው ለምንድን ነው?’’ ብለው ጠይቀው ‘’ በክርስቶስ እና በአቶ መለስ አንድ ስለሆንን ነው’ ብለዋል።
እኝህ ሰው የሃገሪቱንም ህገመንግስት ለመጣስ ምንም የሞራልም ይሁን የአፍ ዳገት አልገጠማቸውም። በንግግራቸው ኢትዮጵያ የማታወቃቸው ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ አሉ’ ብለዋል። መለኪያቸውም እነዚህ ኢትዮጵያውያን አቶ መለስን አለማድነቃቸው ነው። ለእሳቸው ኢትዮጵያ የምታውቃቸው ኢትዮጵያውያን አቶ መለስን የሚወዱ እና የሚያከብሩ ብቻ ናቸው እንጂ በህገመንግስቱ ስለዜግነት የተደነገገው ለእሳቸውም ሆነ ይን ንግግር ሲያደምጡ በጭብጨባ ላጀቡት የስብሰባው አድምተኞች ፋይዳቢስ ነበር። ‘’ በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፡ ይገባል ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።’’ (ዮሃንስ 10፡-9) የሚለውን የክርስቶስ ቃል በሚመስል ንጽረት የኢትዮጵያዊነት ዜግነትን እና በዜግነትም መታወቅን ልናገኝ የምንችለው በአቶ መለስ ስናምን እና አሳቸውን ስንወድስ ብቻ አነደሆነ  ነግረውናል። በኢትየጵያዊነት አንድ የምንሆነውም እንደዛው። ‘መነኩሴው’ ይህን ሁሉ ሲሉ ሌላም የህገመንግስት አንቀጽ እንደጣሱ ግልጽ ነው። ምንም እንኩዋን ፐለቲከኛ እንዳልሆኑ አስቀድመው ቢናዘዙም ቤተክርስቲያንን ወክለው እና ጥቁር ሃይማኖታዊ ልብሳቸውን ለብሰው ባቀረቡት ንግግራቸው ከሁለት የፖለቲካ ጎራወች አንዱን በመደገፍና ሌላውን በማንኳሰስ ሌልኛውን ህገመንግስት- ሃይማኖት በመንግስት/ በፐለቲካው ውስጥ ጣልቃ አይገባም የሚለውን ጥሰዋል።
አንዳንድ ሰወች ግለሰባዊ አምልኮ /personality cult/ እየተፈጸመ ነው የሚሉትን ነገር ተግባራዊ ማስረጃ በሚሆን መልኩ ‘መነኩሴው’ ፈጽመዋል። ምእመኖቻቸውም ይህንንው አብረዋቸው አከናውነዋል። ማን ያውቃል ትላንት አጼ ሐይለስላሴን የሚያመልኩ ሰወች እንደተፈጠሩ አሁን ደግመ አቶ መለስን የሚያመልኩ ሰወች ቢደገሙስ? መነኩሴው በእሳቸው ስም ገዳም ቢያቋቁሙልንስ ምን ይላቸዋል? 
እኒህ መነኩሴ ተሳዳቢም ናቸው። በንግግራቸው ‘’ ዲያሰፖራ ሳይሆን ኤልፎራ ናቸው’’ ብለዋል። ይህ ንግግር ሲፈታ ሁለት አንድምታ ሊኖረው ይችል ይሆናል። የቤተክህነት ሰው ስለሆኑ ቅኔ ተምረው የለ? የመጀመሪያው እንዲህ ወደ አውሮፓ ስደታቸውን ያቀኑትን ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰወች ዲያሰፖራ ብለው እየጠሩ የስደት እግራቸው ወደ አረብ ሃገራት ያቀናውን ሰዎች ደግሞ  ‘ኤልፎራ’ ሲሉ ይደመጣሉ።ሁለተኞቹን በመናቅ ድምጸት። እኝህ ‘መነኩሴ’ አንድም እንዲህ ማድረጋቸው እና ነገሩን እና ስሙን አገላብጠው መጠቀማቸው ሲሆን አንድም በአዲስ አበባ ንብረትነቱ የሼክ አላሙዲን የሆነው ኤልፎራ የዶሮ እርባታ ስም ስለሆነ አቶ መለስን የማይደግፉ ሰወች ዶሮዎች ናቸው ማለታቸው ይሆናል።
እንግዲህ ቤተክህነት ይህን መሰል ጉድ ይዛ፣ ህዝቧን አንድ ባደረገው  ክርስቶስ አንድ ከመሆን ይልቅ በአቶ መለስ አንድ የሆኑ መሪዎች መርተዋት፣ እንዴት ቤተክርስቲያን ትሆነው ይሆን? ለእርሷ ‘’ እኔ መንገድ እና አውነት ህይወትም ነኝ’’ ከሚለው ጌታ ይልቅ ሌላ አውነት ኑሯት እና ይህን የማይቀበሉትን ክርስቲያኖች አግልላና አውግዛ ወዴት ታመራ ይሆን? ግን ግን ክርስቶስ የሞተው እና ለራሱ ቤተክርስቲያንን የዋጀው ‘አውነት በሆኑት’ በአቶ መለስ የሚያምኑትን ብቻ ለመሰብሰብ ይሆን እንዴ?
እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ‘’እውነት’ እና የአንድነት መሰረቷ አቶ መለስ ከሆኑ የእሳቸውን አመራር፣ አመለካከት እና ፖሊሲዎች ያልደገፉ ወይም የተቃወሙ ክርስቲያኖች ክርስትናቸው ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ገባ ማለት ነው።  እኝህ መነኩሴ የብዙ ህዝቦችን ዜግነት እና ሃይማኖታዊ እምነት የሰረዘና ህዝቦች ኢትዮጵያዊ ለመሆንም ሆነ ክርስቲያን ለመሆን እሳቸው የሰበኩትን ‘እውነት’ ለመቀበል በ መለሲዝም መጠመቅ እንዳለባቸው አውጀዋል። ይህ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ንግግር እንዲያቀርቡ በኦፊሴል የላከቻቸው የሃይማኖት አባት የተናገሩትን በአፊሴል እስካላስተባበለች ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ መቀየሩን ማወጁዋን ያረጋግጣል።
ይህ ከሆነ ደግሞ መጻህፍ ቅዱሳዊው አስተምሮ ቀርቶ መደበኛ የሆነው የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሰብ እንኩዋን የሚፈቅደውን ነጻ አስተሳሰብ እንኩዋን በመቃወም ቤተክርስቲያኒቱን አንባገነን የደርጋታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጥንታዊነቷ እና በምስራቅ አፍሪካ ክርስትናን ጠብቃ መቆየቷ የሚወደስ ምግባሯ ቢሆንም ድሮ ለነገስታቱ አሁንም ደግሞ ላሉት መሪዎች አንፋሽ አጎንባሽ መሆኗ አሳሳቢ ነው።
ግን እነዲህ ያለውን ‘’ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች’’ በሚባል ሁኔታ ሰወች በተቁዋማት ላይ የሚፈጽ ሙትን ጥፋት ቤተክርስቲያኒቱ ልታርም ብትነሳ መንግስት በእርግጥ ቅር አይለውም ይሆን?
An Ethiopian Priest speaks at the memorial service of the late PM Melese Zenawi has declared that Mr. Melese is the truth like that of Christ the Lord.

Friday, August 23, 2013

የወጣቱ የመጥለፍ ፖለቲካ በ” ይልቃል አዲሱ ልደቱ…? ” ፀሁፉ ውስጥ


በጥያቄ ምልክትና እና በቃለ አጋኖ የታጀበውን ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” በሚል ርዕስ ወጣት ዳዊት ስለሞን በብዕር ስም /አይናለም/ የተፃፈውን ባለ ብዙ ሀሳብ ፅሁፍ አነበብኩት ፡፡ አንድ ፅሁፍ ሲፃፍ አንባቢ ሊታዘብ ይችላል ሰለዚህ እውነት ላይ እና እየታዩ ካሉ ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር መቃኘት አለበት የሚለው ዋና ጉዳይ በዚህ ፀሁፍ ውስጥ ለኔ አልታየኝም ፡፡ በፅሁፉ ውስጥ አንባቢን ለማሳመን የተደረጉ ውጣ ውረዶች ከመጥቀሴ በፊት ፀሀፊው አባል በሆነበት አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተመለከትኩትን የሚበረታታ ጉዳይ ከማሳሰቢያው እጠቅሳለሁ፡፡
ማሳሰቢያ ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” ፅሁፍ ፀሀፊ ዳዊት ሰለሞን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ኣዘጋጅ ለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአንድነት አባል ስለነገረኝ ከዚህ በታች የምጠቀመው የብእር ስሙን ሳይሆን ዳዊት የሚለውን ዋና ስሙን መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡
መኢአድ ሲባል ኢ/ር ሀይሉ ሻወል፣ ደቡብ ህብረት ሲባል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ፣ ኦብኮ ሲጠቀስ ዶ/ር መረራ ጉዲና… የፖለቲካ ተክለ ሰውነት ለብሰው ብቅ ይሉብናል፡፡ ይህ የፖለቲካ ተክለ ሰውነት በአንድት ውስጥም ግዝፈቱን ሳይቀንስ ተንሰራፍቶበት ቆይቷል፡፡ ይህ ማለትም አንድነት ሲባል በየደቂቃው የሚለዋወጥ አቋም ያለው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እና ባለመልካም ባህሪው ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ድቅን ይሉብን ነበር እነአቶ አስራት ጣሴን አስከትለው፡፡ ወጣት ዳዊትም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች ብለው ከጠቀሱዋቸው መካከል የግለሰብ ተክለ ሰውነት መገንባት አንዱ ነው፡፡
እኔም የግለሰብን ተክለ ሰውነት አንዱ መስፈርት አድርጌ ፓርቲዎችን ስገመግም አንድነት አሁን ካሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የተሻለ ነው እንድል ያደረገኝ ከግለሰብ ትከሻ ላይ ወርዶ አበረታች የሚባል የቡድን ስራ ማክናውን ላይ በመሆኑ ነው፡፡
የተመለከትኩትን ጠንካራ ጎን ከገለፅኩ በኋላ የፓርቲው አባል የሆኑት ወጣት ዳዊት ፅሁፍ ላይ ላተኩር፡፡ ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅ ያደረገውን ጥረት በማድነቅ ፅሁፉ መጀመሪያ ላይ የጠቀሱት የደርግ/ የኢህአፓ /የመኢሶን ፖለቲካዊ መጠላለፍ ዛሬ ላይ እንዲመጣ ወይም ዛሬ ላይ ያለው የመፈራረጅ ፖለቲካ እንዲቀጥል ታጥቀው የተነሱ ነው የሚመስለው፡፡ እንዴት! ማለት ጥሩ….. በአዲስ መስመር ከመቀጠሌ በፊት እኔ የሰማያዊ ፖርቲ አባልም ደጋፊም አለመሆኔ ሊታወቅ ይገባል፡፡
አንባቢን ለማሳመን እና ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ስብስብ መሆኑን ለማጣጣል የአቶ ልደቱ ወጣት መሆን በመጥቀሥ በጥሩ ሁኔታ እየተቀሰቀሰ ያለውን ፖለቲካ ለመጥለፍ ‹‹አዲሶቹ ጎጆ ወጪዎች ከመጀመሪያው ቤታቸው ሲወጡ በአብዛኛው ባዶ እጃቸውን አይሆኑም፣የእናት ፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፕሮግራም፣አደረጃጀትና አባል ይዘው ሹልክ ይላሉ፡፡ለዚህ እንደምሳሌ ኢዴፓና ሰማያዊ ፓርቲን መውሰድ ይቻላል፡፡›› ይሞክራሉ፡፡ እኔም አንድ የመጥለፉ መንገድ ልከተልና ፀሀፊውን ልጠይቀው፡፡ ቅንጅት የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነው፡፡ መሪዎቹ ታስረው ሲፈቱ በጋራ መቆም አቃታቸውና የየራሳቸውን ደጋፊና አባል በመያዝ ለአራት ተሰነጣጠቁ፡፡ከግንቦት 7 በስተቀር ሁሉም የሰላማዊ ትግል መርጦ የቅንጅቱን መንፈስና ፕሮግራም ለማስቀጠል በያለበት ይንቀሳቀሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንድነት አንዱ በመሆኑ የእናት ድርጀቱን አባል ፕሮግራም ይዞ ሹልክ አለ ማለት ነው ወይስ አንድነት የተለየ ፕሮግራም አረቀቀ? ይህን ለመመለስ የቅንጅትንም የአንድነት በደንብ ፕሮግራሞች ማየት ያስፈልጋል እንዳትረሳው!
የሰማዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ላይ ያስቀመጠው ቅሬታ / ግን ሰይጣናዊ ቅናት ብለው በትክክል ይገልፀዋል/ ጠቅለል አርጌ ለመግለፀ በሁለት መክፈል እፈልጋለሁ፡፡ ሊቀመንበሩ ላይ የቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ በሚል እና ፀሀፊው ጎልቶ ለመውጣት ባለው ጉጉት የሚከተላቸው መንገዶች በሚሉ ፡፡
ለፖለቲካው በማሰብ
ኢ/ር ይልቃል /የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር/ “ፓርቲዎች አሉ ብለን አናምንም ተባበሩ የምትለን ከማን ጋር ነው ? መድረክ ምን ሰራ አንድነትና መድረክ እየተባሉ አይደለም? አንድነት ውስጥ የገባው ብርሃን ወጥቷል እኛ ከማን ጋር እንተባበር ? ብለዋል ብሎ ወጣት ዳዊት ይኮንናል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ንግግር ላይ ያለውን ስህተት ለማሳየት ፓርቲዎቹ የሰሩትን ምንም መረጃ ማቅረብ ስላልቻለ በደፈናው በህብረት ለመስራት አንፈልግም ብለዋል ሲል ተንከባሎ ያልፋል፡፡ የመድረክ አባል ፓርቲዎች የደቡብ ህብረት ከፕ/ር በየነ ሳምሶናት ውስጥ መውጣት ሳይችል፣ ኦፍዴን ከአቶ ቡልቻ የግል ንብረትነት ሳያልፍ፣ ኦብኮ ከዶ/ር መራራ የኮሜዲ ምሽት ሳይላቀቅ ፣አረና አባላቱ በነፃ ዝውውር ለሰማያዊ ፓርቲ እየፈረሙ ባሉበት ሰአት እና አንድነት በኣዛውንቶችና በወጣቶች መሀክል በሚደረግ ገመድ ጉተታ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ከማን ጋር በህብረት ይስራ ነው የሚባለው፡፡ በተጨማሪም ብርሀንም ከአንድነት የወጣው ገመድ የጉተታ ውጤት ይዞት የሚመጣው ጦስ አስግቶት ነው፡፡ ታዛቢ ስላለ እውነቱ ይህ መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አደለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡
በተጨማሪም አንድነትን ጨምሮ ሁሉም የመድረክ ፓርቲዎች ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም ስለሌላቸው መስማማት አልቻሉም ፡፡ ይህንን ስል በስሜት አለመሆኑን ለማስገንዘብ ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ የመሬት ጥያቄና የመገንጠል መብት ፓርቲዎቹ ከግንባርነት እንዳያልፉ ማነቆ ሆነው ስራ እዳይሰሩ ያደረጋቸውን ብቻ ማንሳት በቂ ነው፡፡ ይህም እውነት ሲገለጽ በሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አይደለም ለማለት እገደዳለሁ፡፡
ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ከላይ እንደጠቀስኩት ከግለሰብ ስብእና ራሱን በማፅዳት የቡድን ስራን በመጀመር የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የቡድን እንቅስቃሴ ባለፉት ግዚያት እንደተመለከትነው በተለያዩ የክልል ከተሞች በመንቀሳቀስ የቀዘቀዘው የህዝብ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዲያንሰራራ ሚዛን የሚደፋ አስተዋፆ አድረጓል፡፡ ለዚህም አበረታች ጅማሮ ከፊትም ከኋላም በመሆን ከፍተኛ አስተዎ ያደጉትን ግርማ ፣ዳንኤል እና በላይን የመሰሉ ወጣት ፖለቲከኞችን ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ በዛውም ልክ ይልቃል ጎልቶ ለመውጣት ይፈልጋል ተብሎ እንደተከሰሰው በአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄም ውስጥም በበርካታ ወጣቶች ላይ ጎልቶ የመታየት ፍላጎት ሲከሰት ከርሟል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወጣት ዳዊት ይግኝበታል፡፡ እንዴት የሚል ጥያቄ ከተነሳም መልሱን ክዚህ በፊት ወጣቱ የሚያድጋቸውን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ድርጊቶች ላሳይ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የተመለከታቸውን ህፀፆች እንደጋዜጠኝነቱ እንዲታረሙ በበሳል ብእሩ ሲጠቁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የጋዜጠኛውን ጥቆማ በመቀበል የታዩትን ችግሮች ለማረም ደፋ ቀና ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ የተባለው ብሂል በወጣቱ ዳዊት ላይ ተተግብሮ ‹‹ ተመስገን ደሳለኝ ሲያዳልጠው›› በሚል ጽኁፍ በአደባባይ ፓርቲውን ለምን ነካ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት እፍኝ እውቅና ለማግኘት ሲታገል መድከሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህ ተግባር በተመስገን ላይ ብቻ የተገደበ እይደለም ፡፡ ብዙ መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን ዝም በመባሉ ያሸነፈ ስለመሰለው በተመሣሳይ ላሞኛችሁ አይናችሁን ጨፍሁ ብሎ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ ሲዘምት ጎልቶ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የሚቀዘቅዘው የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ስላሳሰበኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡
በአጠቃለይ የወጣቱ ፅሁፍ ለሀገራችን ፖለቲካ በማሰብ የቀረበ ሀሳብ ሳይሆን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ የተጀመረው የህዝብን የማንቃት ስራ አዳክሞ ሀገሪቱን በአንባገነንነት ለሚመራው ኢህአዴግ ነው የሚጠቅመው፡፡ ስለዚህ ወጣት ዳዊት ገና ብቅ ብቅ የሚሉ ወጣት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ በመፃፍ እውቅናን ለማግኘት ከመጣር ከላይ በአንድነት ውስጥ ከባድ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉትን ምሳሌ በማድረግ ስራቸውን ማጉላት ላይ ብታተኩሩ ወይንም እነሱ ልምድ ካላቸው ፖለቲከኞች ጀርባ ሆነው ልምድ ቀስመው ዛሬ ለሀላፊነት የበቁበትን መንገድ መከተል በሳልነት መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፡፡ በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ መስመር…
ምስረታ ጀምሮ አወዛጋቢ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ 8 አመት ሙሉ የቀዘቀዘውን የሀገሪቱ ፖለቲካ ሚዛን በሚደፋ መልኩ ለማሞቅ ( ለማንቀሳቀስ) ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እና በፓርቲው ውስጥ ያሉት አመራሮች ከሊቀ መንበር ውጪ ያላቸው የፖለቲካ ብስለት በሰፊው ለህዝብ ስላላደረሰ አውዛጋቢነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል ፡፡ ይህም የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እንዲሁም በፓርቲው ውስጥ ያሉት ወጣት አመራሮች ያላቸው የፖለቲካ ብስለት ለሰፊው ህዝብ ካልደረሰ በሀገራችን ለዘመናት ለቆየው የመጠለፍ ፖለቲካ ጭዳ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ በተጨማሪም እንታገልለታለን ለምትሉት ህዝብ የማሳወቅ ፓርቲው ግዴታም አለበት፡፡
Mastewal  Brihsnu

Thursday, August 22, 2013

ሰበር ዜና በአሜሪካ ግቢ ቦምብ እላያችን ላይ ሳይፈነዳብን ተገኘልን



በአሜሪካ ግቢ ቦምብ እላያችን ላይ ሳይፈነዳብን ተገኘልን

"
ምስጋና ለኢትዬጲያ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሄራዊ መረጃ እናደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የጸረ ሽብር ቡድን ግብረ ሃይል" 
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ከተማ በተለምዶ በአሜሪካግቢ ራስ ስዩም ሆቴል አጠገብ ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭነትየሚጫንበት ቦታ አካባቢ በሚገኘው ራህመት ኤጀንሲ በር ላይ ኮድየታርጋ ቁጥር 73189 በሆነ አንድ |የጭነት ማመላለሻ አይሱዙጎማ
ስር የአጅ ቦምብ ተገኘ ተባለላቹ፡፡፤ ይህን የእጅ ቦምብ የአዲስአበባ ከተማ መደበኛ ፖሊሶች ቀደም ብለው በእጃቸው ይዘውትእንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፤የእጅ ቦምቡን ጠዋት ይዘውት ከነበሩት ሁለት ፖሊሶች መካከል የአንዱ ፎቶ ከዚህበታች ተያይዞ ቀርቧል|፡፡ሙስሊሙ የመረጃ ሰው ሆኗል፡፡አልሃምዱሊላህ ይህ ቦምብ አፈንጂው እና ቦምባ አምካኞችያደረጉት ትንቅንቅ አንድ ወንድም ያደረሰኝን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡ የተቀረውን መረጃ በቦታው ከነበሩ እና ከኢቲቪ ማጣራትትችላላችሁ

"
አንድ ግለሰብ ቦምብ ይዞ በመምጣት አንድ የጭነት መኪና ጎማ ስር ቦምቡን አስቀምጦ ዞር ይላል፡፤ በመቀጠልም ይህግለሰብ ከቆይታዎች ቡሃላ ተመልሶ በመምጣት እዛው አካባቢ ይቆማል፡፡ በመቀጠልም ፖሊስ ይህን ግለሰብ በቁጥጥር ስርያውለዋል፡፡ከዛ ፖሊስ ይህን ግለሰብ ሲፈትሸው ሌላም ቦምቦች በኪሱ ስር ያገኛሉ፡፡ ከዛ የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊመረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ይህን አሸባሪ ግለሰብ በህዝብ እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርስበቁጥጥር ስር አዋሉት፡፤
ከዛ የፈንጂ አምካኝ ግብረሃይል መጣና መኪናው ጎማ ስር የተቀመጠውን ቦምብ እንዳይፈነዳ በጥንቃቄ በማድረግ አክሸፈው፡፤ከዛ በቃ ድራማው በሚገርም ሁኔታ በመጠናቀቁ ቀረጻ ተካሂዶለታል፡፡ በጥሞና ስላነበባችሁልኝ አመሰግናለው"
ቆይ ትንሽ ልጨምርላችሁ ይህ አሸባሪ ግለሰብ እራሱ ያስቀመጠው ቦምብ ጋር በመምጣት መፍንዳት እና አለመፈንዳቱንየሚጠባበቀው ምንኛ አስገራሚ አሻባሪ ነው???? ቀጥሎም ለሌላ ተልኮ የሚሆን ቦምቦችን በኪሶ ሸክፎ ይዞ ነበር፡፤ይህንንምአደገኛ ሊፈጸም የነበረውን የሽብር ጥቃት በማስመለከት ለኢቲቪ ዜና የሚሆን ድራማ ይህ አሸባሪ ግለሰብ ከፌደራል ፖሊስእና ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረ ሃይሉ ጋር በመሆን ሲከውን እንደነበር የአይን እማኞችገልጸዋል፡፡ የዚህን ሙሉ ዜና ዝርዝር ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ ይጠብቁ:;
ከዚህ ቀደም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያም ተመሳሳይ ጠቀጣጣይ የሆኑ ሁለት ስሊንደሮች ተቀምጠው መገኘታቸው ኢቲቪዘግቦልን ነበር፡፡ደሞ ሌላ ቀን ምን አይነት ነገር መያዡን እንሰማ ይሆን???? ፡፡
ምናለ ኢትዬጲያ ሃገሬ ለአለም ሰላም ሁሌም በምታደርገው ጥረት የምትደነቅ በመሆኗ እንዲህ አይነት የፀረ ሽብር ግብረሃይሏን ችሎታ ለሌሎች ሃገሮችም ልምዷን ብታካፍል እና ቦምቦች ሳይፈነዱባቸው ሁሌም ከነአሸባሪው በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ ብትረዳቸው ?????
እኔስ ምንም አልልም ግን ብቻ ይሄ ድራማ እንዲ እያጃጃለን አንድ ቀን የምር አፈንድተውት እንዳይጨርሱን እሰጋለው!!!
ለማንኛውም ቦንቦቹ ሳይፈነዱ በቁጥጥር ስር ስለዋሉ አልሃምዱሊላህ በዚህኛው ድራማ ሂወታችንን አልቀጠፉብንም፡፡
አላህ የኢትዬጲያን ህዝብ ለድራማ ተብሎ ከሚደረስ ጥቃት ይጠብቅልን!!!!