Saturday, June 29, 2013

የናይል ተፋሰስ ሚኒስትሮች ተሰበሰቡ [voa]


የናይል ተፋሰስ ሚኒስትሮች ተሰበሰቡ [voa]

ባለ አምስት ቢሊየን ዶላር መዋዕለ-ነዋዩ ኅዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ጎረቤቶች ቀልብ አነቃቅቶና ውዝግቦችም እየተሰሙ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ በአባይ ውኃ አጠቃቀም ላይ ለመምከር የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ድርጅት ስብሰባ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ላይ ዛሬ ተሰብስበዋል፡፡

የኅዳሴ ግድብ ወደ ግብፅ የሚወርደውን ውኃ መጠን ይቀንስብናል ሲሉ ግብፃዊኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሥጋታቸውን በየጊዜው እየገለፁ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ ግንባታ ሥራ እንደማታቆም አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማንንም ሃገር የመሻሻል ዕድል እንደማትቃወም የተናገሩት የግብፅ የውኃ ኃብቶች ምክትል ሚኒስትር አሕመድ ባህ ኤልዴይን ይሁን እንጂ ናይል ወንዝን በተመለከተ ማንኛቸውም ዕቅዶች ከመነደፋቸው በፊት መዘዞች ሁሉ ግምት ውስጥ ሊገቡ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡


No comments:

Post a Comment