Wednesday, July 31, 2013

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በግብረ ሰዶማዊያን እያሳዩ ያለው ተገቢ ያልሆነ እንክብካቤና መስፋፋት ልንቃወመው ይገባል፡፡


ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖምን እንቃወማቸው!!
አዲሷ የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ ውስጥ ግብረ ሰደማዊነት ተቀባይነት እንዲያገኝ አጠንክራና ቅድሚያ ሰጥታ እንደምትሰራ መናገሯ በጣም አሳስቦኛል፡፡በተለይ ይህ አባባል በሀገሪጻውስጥ ባሉ ቤተ እምነቶችና የሀይማኖት አባቶች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን አይቀርም፡፡መጀመሪያ እረኛውን በለው ከዛ በጎቹ ይበተናሉ በሚለው ስልት ማለት ነው፡፡ እስካሁን ባለው ተሞክሮ ግብረ ሰዶማዊነት በአውሮፓና በአሜሪካ ለማስፋፋት በጣም እየተጠቀሙበት ያለው ስልት መጀመሪያ የሀይማኖት አባቶችንና ቤተእምነቶች በመንደፍ ነው መንጋውን መበከል የሚል አካሄድ ነው፡፡ለዚህም ጥሩ ምሳሌው አዲሱ የሮማ ጳጳስና የደቡብ አፍሪካው ዴዝሞን ቱቱ የተባሉ የሀይማኖት ቆብ የደፉ አባቶች በክርስትና ላይ የፈጸሙትና ዝሙት ማስዋል ተገቢ ይመስለኛል፡፡በተያያዘም የኢትዮጵያ መንግስ በተለይ የውጪ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በግብረ ሰዶማዊያን እያሳዩ ያለው ተገቢ ያልሆነ እንክብካቤ ልንቃወመው ይገባል፡፡የመንግስት ሚዲያዎች በሙሉ፣ ግብረ ሰዶማዊያን በህዝቡ ላይ እያደረሱ ያለው በደልና እያዛመቱ ያለውን በሽታ፣እንዳይዘግቡ የተከለከሉበት ምክንያት፣ዶክተር ቴድሮስ በነጮች ዘንድ ያላቸውን ከበሬታ የግብረ ሰዶማዊያንን አጸያፊነት መማጋለጥናበመታገል ማጣት የፈለጉ አይመስሉም፡፡
Gay gathering sparks row between Ethiopia’s churches and state
By Reuters Staff
November 29, 2011
ethiopia africa aids conference church state muslim orthodox christian catholic protestant
(Children run past a mural painting of an Aids ribbon at a school in Khutsong Township, 74 km (46 miles) west of Johannesburg, August 22, 2011. REUTERS/Siphiwe Sibeko)
A meeting organised by an African gay lobby group ahead of an AIDS conference in Ethiopia has sparked a rare spat between the government and religious groups. Religious leaders demand the cancellation of the gathering scheduled for Saturday, organised by African Men for Sexual Health and Rights, saying it would violate the country’s conservative culture.
State officials, however, are unwilling to budge having lobbied hard to win hosting rights for the influential 16th International Conference on AIDS and STIs in Africa due to start a day later.
On Tuesday, Abune Paulos, partriarch of the Ethiopian Orthodox Church, joined the Muslim mufti and the heads of the Catholic and Protestant churches for a meeting before delivering scathing remarks about homosexuals to the media.
Young church activists handed out dossiers railing against the weekend meeting on “men who have sex with men (MSM) in Africa and HIV”, which is scheduled to feature presentations from 15 experts. “We were prompted to sound this alarm after this group launched immoral activities that would tarnish and dirty our culture,” read part of the dossier.
Health Minister Tedros Adhanom met the religious leaders but made no denunciation of the gay group’s gathering. Abune Paulos afterwards told reporters: “We will continue to pray.”
Homosexuality is taboo in many African nations. It is illegal in 37 countries on the continent, including Ethiopia, and activists say few Africans are openly gay, fearing imprisonment, violence and loss of jobs. Homosexual acts in Ethiopia carry penalties of imprisonment of up to 15 years.
Religious leaders, including Abune Paulos, have in the past called for a constitutional ban on homosexuality, which they once termed “the pinnacle of immorality.”
“For people to act in this manner they have to be dumb, stupid like animals,” he told reporters in 2008. “We strongly condemn this behaviour. They have to be disciplined and their acts discriminated, they have to be given a lesson.”
በ 1 7 ህ ፃ ና ት ላ ይ ግ ብ ረ ሰ ዶ ም የ ፈ ጸ መ ው መ ም ህ ር ተ ፈ ረ ደ በ ት
በአሸናፊ ኃይሌ
ሐምሌ 16 ቀን 2005 ዓ.ም
ፖሊስ እና እርምጃው ጋዜጣ
ትምህርት ቤቶች የዕውቀት ገበያ፣የጥሩ ፀባይ መሸመቻ መሆናቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ የዕውቀት አባት የሆነው መምህርም በትምህርት ቤት ያለው ኃላፊነት ከባድና ዘርፈ ብዙ የመሆኑን ያህል ክብሩና ሞገሱም የዚያኑ ያህል ከፍ ያለ ነው፡፡ መ ም ህ ሩ የዶክተሩ፣የኢንጅነሩ፣የአብራሪው፣የሾፌሩ አባት ነው፡፡ ማነው ያለመምህሩ ድጋፍ አንቱ የተባለ፡፡ በዚህ የጥሩ ምሳሌ ዓለም ውስጥ በሚገኘው መምህር ሽፋን አንዳንድ ግለሰቦች መልካም ስሙን የሚያጎድፍ በስመ አስተማሪ የሚነግዱ ሲገኙ መኮነንና ማውገዝ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በስልጤ ዞን በአዳዞር ሸበል ቀበሌ ቡጫ አንደኛ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ውስጥ የተፈፀመው ተግባር ለመንገር የሚዘገንን ለመስማት የሚቀፍ ቢሆንም ከዚህ ዓይነቱ ብልሹ ምግባር መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ እውነታውን ማወቅ ግድ ይላል፡፡
ድርጊቱን ፈጽሟል በሚል ክስ የቀረበበት መምህር ሙሉጌታ መንግሥቱ የተከሰሰበት ፍሬ ነገር ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች መካከል በ17 ታዳጊ ሕፃናት ላይ ግብረ ስዶም ፈጽሟል በሚል ነው፡፡ የስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፖሊስ እንደገለፀው ተከሳሹ ይህን አስፀያፊ ተግባር ሊፈፅም የቻለው ተማሪዎቹን አንድ በአንድ መኖሪያ ቤቱ ድረስ እየወሰደ በታዳጊዎቹ ላይ ጥቃቱን አድርሶ ለሰው እንዳይናገሩ በማስፈራራት ገመናው እንዳይጋለጥ ያደርግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ድርጊቱ መደጋገሙና ጥቃት ደርሶባቸው በህመም የሚሰቃዩት ታዳጊ ሕፃናት ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ ድርጊቱ ይፋ እንዲወጣ ምክንያት ሆኗል፡፡ ልጆቻቸው ባልታወቀ ህመም ሰቃየታቸው ያሳሰባቸው ወላጆች ልጆቻቸውን በማግባባትና በማበረታታት የሚደርስባቸውን ስቃይ እንዲነግሯቸው ባደረጉት ጥረት እውነታውን ለማወቅ ችለዋል፡፡የሕፃናቱ ቤተሰቦችም ከልጆቻቸው አንደበት የሰሙትን ለወረዳው ፖሊስ በመግለፃቸውና ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ ተቀብሎ ባደረገው ማጣራት በግለሰቡ ላይ በቂ ማስረጃ ማሰባሰብ ችሏል፡፡ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ መዝገብ በማስረጃ አስደግፎ የወረዳው ፍ/ቤት እንዲመለከተው አድርጓል፡፡ የወንጀሉን ፍሬ የተመለከተው የወረዳው ፍ/ቤት ተከሣሽ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል የተፈቀደለት ቢሆንም የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጧል፡፡
ፍ/ቤቱም ሰኔ 27 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ነው ሲል የፈረደበት መምህር ሙሉጌታ መንግሥቱ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል ም/ኢ/ር ከማል ሳላህ የላከው ዘገባ ያስረዳል፡፡ ከዚህ ዓይነቱ አፀያፊና አሰቃቂ ተግባር ወላጆችና አሳዳጊዎች በቀላሉ ለጥቃት የሚጋለጡትን ሕፃናትና ታዳጊ ልጆች መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የልጆችን ውሎና አዳራቸውን መከታተል፣ ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸውን አንዳንድ ግለሰቦችንም በትኩረት መመልከት የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ freedom4ethiopian.wordpress.com

የሥላሴዎች እርግማን፤ (አንድ) አዳክሞ ማደህየት pr. መስፍን ወልደ ማርያም


ff049-mesfin-woldemariam
አዳክሞ ማደህየት የወያኔ ትልቅና ዋና መሣሪያ ሆኖ አገልግሎአል፤ ወያኔ ከኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አርባ ያህል መምህራንን ያስወጣው ገና በጠዋቱ ነበር፤ ከቴሌ ከመብራት ኃይልና ከባንክ ሰዎችን እየመነጠረ ያስወጣው በዘር አመካኝቶ ቢሆንም በትምህርታቸውና በልምዳቸው የጠጠሩበትን ሰዎች እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ እንደፐሮፌሰር ዓሥራት ያለውን በሁለት የታወቁ የእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች የተመሰከረለትን ሰው በችሎታ ማነስ ብሎ ማስወጣት ችሎታ ያነሰው ማን አንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል፤ እነዚህን የተለያዩ ባለሙያዎች በማስወጣት ወያኔ ሰዎቹን አልጎዳም፤ ሁሉም የተሻለ ኑሮና የተሻለ የሥራ እርካታ አግኝተዋል፤ የተጎዱት መሥሪያ ቤቶቹ ናቸው፤ ከወያኔ ጋር ወደኋላ የሄደችው ኢትዮጵያ ነች፤ ወደኋላ የሄደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።
በመሬት ያየነው እንደሆነ የወልቃይት-ጸገዴና የራያ-ቆቦ ድንበር ለትግራይ በሚጠቅም መልኩ ቢለወጥና ጎንደርንና ወሎን ቢያስቀይምም አዲስ የመሬት ድልድልን ፈጥሮአል፤ ከመሬቱም ጋር የ‹‹አማራ›› ሕዝብ ቁጥር እንዲቀንስ ሆኖአል፤ ይህ ሁሉ ማዳከም አይሆንም? አዳክሞ ማደህየት አይሆንም? ምርጥ የአገሪቱ መሬት ለውጭ አገር ባለሀብቶች በቸርነት የሚቸበቸበው ገበሬውን ለማዳከምና ወደኩሊነት ለመለወጥ አይደለም? ወደኩሊነት በመለወጥ የራሱን ዕድል በራሱ በመወሰን ፋንታ ሌላ ሰው፣ ምናልባትም ባዕድ ይወስንለታል፤ ከዚህ የበለጠ አዳክሞ ማደህየት ምን አለ?
አንድን ሕዝብ ካዳከሙ በኋላ ማደህየቱ በጣም ቀላል ነው፤ ደርግ ባያውቅበትም በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ሰይፍ ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሞክሮ ነበር፤ የደርግ ችግር ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሀብታሞቹን በጠመንጃ ማደህየት ግዴታ አድርጎ መከተሉ ነበር፤ መሬት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ነው ብሎ አላቆመም፤ ወይም በባለቤቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም መሬትን ለውጭ አገር ሰዎች አልቸበቸበም፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ አደላደለ፤ የቤት ኪራይን ቀነሰ፤ በኅብረት ቤት ለመሥራት ለሚፈልጉ ሁሉ መሬቱንም ሆነ ገንዘቡን በቀላሉ የሚያገኙበት ሥርዓትን አመቻቸ፤ ብዙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቻሉ፤ ደርግ በጠመንጃ ደሀነትን ለማጥፋት ሲሞክር ሀብታሞች መቃብሩን ቆፈሩለት፤ ወያኔ ደግሞ ሀብታምነትን በጠመንጃ ለመትከልና ደሀነትንም በጠመንጃ ከአገር ለማስወጣት ሰፊ እቅድ አውጥቶ እየሠራበት ነው፤ ወያኔ መሬት የግል የሚሆነው በመቃብራችን ላይ ነው በማለት ተንብዮ ነበር፤ ትንቢቱ ከደረሰ ቀባሪዎቹ ደሀዎች ሳይሆኑ አይቀሩም።
ወያኔ ሕገ መንግሥቱን አሳምሮ የመደራጀት መብትን ከሥራ ውጭ በማድረግ የሠራተኞች ማኅበርን፣ የመምህራን ማኅበርን፣ የነጻ ጋዜጠኞች ማኅበርን፤ የገበሬ ማኅበርንና ሌሎችንም በቁጥጥሩ ስር አደረጋቸው፤ አዳከማቸው ማለት ነው፤ እነዚህ ሁሉ ማኅበሮች ዛሬ ነጻ ህልውና የሌላቸው፣ ነፍስ የሌላቸው አካሎች ናቸው ለማለት ይቻላል፤ የሴቶች ማኅበርና የወጣቶች ማኅበር የሚባሉትም ሁኔታቸው ያው ነው፤ የተለያዩ የማኅበረሰብ ድርጅቶችም እንደእድር ያሉ ባህላዊ የሆኑትም ጭምር ወይ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ወይ ከሥራ ውጭ ሆነዋል፤ የፖሊቲካ ፓርቲዎችና ነጻ ጋዜጦች አሜሪካ በሽብርተኛነት ላይ ጦርነትን እስቲያውጅ ድረስ አሜሪካንን ለማባበያ ጠቅመው ነበር፤ ኢትዮጵያ የአሜሪካ ረዳት ሆና በሽብርተኞች ላይ በሚደረገው ጦርነት ላይ ከአሜሪካ ጋር መሰለፍ ስትጀምር የኢትዮጵያ የፖሊቲካ ፓርቲዎችና ነጻ ጋዜጦች የአሜሪካን የይስሙላ ድጋፍም ማጣት ጀመሩ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም የፖሊቲካ ፓርቲዎችና ነጻ ጋዜጦች አፈና በከፋ መልኩ ተጀመረ፡፡
በሃይማኖት በኩል ያየነው እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቁጥጥር ስር የዋለችው ገና ከመጀመሪያው ነው ለማለት ይቻላል፤ እንዲያውም በቅርቡ የቀድሞው የወያኔ መሪ እንደተናገረው የወያኔ ተዋጊዎችን መነኮሳት እያስመሰሉ በየገዳሞቹ ሰግስገው እንደነበረ አውቀናል፤ ስብሐት ነጋም ጳጳሳቱ ውስጥ ‹‹አንድም ሰው የለም፤ ቢገኝ አንዲሸለም አደርጋለሁ፤›› ብሎ በአደባባይ ሲናገር ቆብ ጭነው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሰፈሩት ሁሉ ከመምህራን ማኅበርና ከሠራተኞች ማኅበር ሹሞች የማይሻሉ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አስመስክረዋል፤ አሁንም በመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ላይ የሚፈጽሙት የሚያሳየው የመንፈሳዊ አባቶችን ጠባይ ሳይሆን የጉልበተኞችን ማንአለብኝነት ነው፤
ለካህናትሰ ሰመዮሙ ጼወ፤ ወዓዲ ለካህናትሰ ሰመዮሙ ማኅቶተ፤ ካዕበ ሰመዮሙ ብርሃኖ ለዓለም፤ ወካዕበ ሰመዮሙ ጸሐየ ዘያበርህ ጽልመተ እንዘ ክርስቶስ ጸሐየ ጽድቅ ውስተ አልባቢሆሙ፤ ወካህንሰ ዘቦቱ ልቦና ይገሥጾ ለንጉሥ በእንተ ምግባራት ዘርእየ፤ … ክብረ ነገሥት
ይህንን ትእዛዝ ለመፈጸም ቃል ኪዳን የገባ ሰው ማንም ቢሆን ጥፋት ሲሠራ ከተመለከተ ‹‹ስደትንም ሆነ ሰይፍን ሳትፈራ›› ተቆጣው የተባለና ሥልጣን የተሰጠው ካህን እንዲያውም የጥፋቱ ተሳታፊ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ተልእኮ ማስተላለፍ አትችልም፤ በዚህም ምክንያት መሳለቂያ እየሆነች በሌሎች ባልተሻሉ ቤተ ክርስቲያኖች እየተገፋች ነው።
በእስልምናውም በኩል መንፈሳዊ መሪ ነጥሮ ሊወጣ አልተቻለም፤ ምእመናኑም እምነታቸውን እነሱ በፈለጉት መንገድ ለማስተናገድ ባለመቻላቸው ለመብታቸው ሲታገሉ ዓመት አለፋቸው፤ አሁንም እየታገሉ ነው፤ በእስልምናውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኩል ያለው ቸግር ተመሳሳይነት ቢኖረውም የእስልምና ምእመናኑ በትግል ጥንካሬ በጣም ልቀው ሄደዋል፤ የትግሉ አካሄድ ግን እንቅፋቶች እያጋጠሙት በመሆኑ ጠመዝማዛ የሚሆን ይመስላል።
ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በጎሣ ላይ አተኩሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከፋፈል በአጠቃላይ ሲታይ ያልተከፋፈለበት ነገር የለም፤ የሁለተኛ ደረጃን ትምህርት በጣም አዳክሞ የስም ዩኒቨርሲቲዎችን በቁጥር የበዙ በማስመሰል ትምህርትን ማዳከሙ ዋናና መሠረታዊ ነው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም በማናቸውም ዓይነት ማኅበራዊ ጉዳይ በነጻነት መደራጀትን አንቆ በመቆጣጠር ሕዝቡ መፈናፈኛ እንዳያገኝ አድርጎት ቆየ፤ ሌላውን ሁሉ መንገድ መቆጣጠሩ ከሞላ-ጎደል የተሳካ መሰለ፤ አሁን መጨረሻው ላይ የሃይማኖት ጉዳይ ከረር እያለ መጣ፤ ሰው ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት ለሃያ አንድ ዓመታት በማሻከርና በማዳከም ከፍተኛ ጉዳትን አደረሰ፤ አሁን ደግሞ ሰዎች ከፈጣሪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻከርና ለማዳከም ቀድሞ የተጀመረው የቁጥጥር ጥረት አይሎ በአደባባይ ወጣ፤ በዚህ ጊዜ እንዳጋጣሚም ለወጉም ቢሆን ሃይማኖት ያለው ሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ክብረ ነገሥት ‹‹እግዚአብሔርን ፈሪና አስተዋይ ካልሆነ አለቃ ይሆን ዘንድ አይገባውም፤›› ይላል።
በአገር ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከላይ በአጭሩና በአጠቃላይ እንደተገለጸው ከታትፈው በቁጥጥራቸው ስር አድርገው እያሹ አዳከመው አልጋ ላይ ካዋሉት በኋላ ስደተኛውን እየመለመሉ በመሬትና በተለያዩ መደለያዎች እያባበሉ እየተስገበገበና እየተክለፈለፈ የሚገብርላቸውን አገኙ፤ እንዲህም ስደተኛውን በቤተ ክርስቲያን ሳይቀር ከፋፍለው አዳከሙት፤ የተዳከመ አይታገልም፤ ቢታገልም አያሸንፍም።
የተሸነፈንና የተዳከመን ሁሉ በኩርኩም ማደህየቱ ቀላል ነው፤ ነገር ግን ሁሉም ተከታትፎ ለመሸነፍና ለመደህየት የበቃው በወያኔ ኩርኩም ብቻ ሳይሆን በራሱ ስግብግብነትም ጭምር ነው፤ የሥላሴዎች እርግማን!

Tuesday, July 30, 2013

አስከፊው ስርዓት ከውስጥም ከውጭም ተወጥሯል።

አስከፊው ስርዓት ከውስጥም ከውጭም ተወጥሯል።

አበራ ሽፈራዉ /ከጀርመን/
የኢትዬጵያን ሕዝብ ሰብአዊና ቁሳዊ መብቶች በነፆነት ትግል ሰበብ ሕወሐት ለአለፉት 39 ዓመታት ሲረግጥ ቆይቷል።በመግቢያዬ ላይ ሀሳቤን በዚህ መልክ እንዳጠቃልል ያደረገኝ ደግሞ ባለፉት 39 ዓመታት የተከናወኑትን መለስ ብዬ ሳያቸው ከሰመሗቸው፣ካየሗቸውና ካነበብኳቸዉ እንደተረዳሁት በእርግጥም  ኢትዬጵያውያን በነዚህ ዓመታት በሕወሐት የለየለትና መሰሪ ተግባር  የተነሳ ሲገደሉ፣ሲታሰሩ፣ሰብዓዊ መብታችን ሲረገጥና፤በነፆነት ሥም ብዙዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሕወሐት ጥቅም አስፈፃሚነት ሲሞቱ አልያም የጥቅሙ ተቀናቃኞች በሙሉ ሕይወታቸዉን ሲያጡ ቆይተዋል፤አለፍም ካለ ደግሞ ያፈሩትን ንብረትና ሀብትም ለማጣት ተገደዋል፣ተዘርፈዋል፣ ተነጥቀዋል ፤እምቢ ካሉም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከዚህ አለም በጥይት ተገድለው በሞት ተለይተዋል ።
ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላም ለ22 ዓመታት የታየው ተጨባጭ ሁኔታ በርግጥም እነዚህ ሕወሐቶች የኢትዬጵያ ቀንደኛ ጠላቶች መሆናቸውን አለምንም እፍረትና ይሉኝታ ሲያቅዱና ሲተገብሩ ቆይተዋል፤አሁንም ቀጥለዋል፤ተዉ ያለም የሚጠብቀው እስር፣ግርፋት፣መሰደድና ሞት መሆኑ ለሁሉም ኢትዬጵያውያን ብቻ ሳይሆን ዓለም እያወቀው ያለ ጒዳይ ሆኗል።
የውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲና የውጭ ግንኙነቱም በተወሰኑ የጥቅም ግንኙነት ላይ ብቻ ባተኮረና የኢትዬጵያን ሕዝብ ጥቅም ወደጐን በተወ መልኩ የተከናወነ ሆኖ ቆይቷል፤በውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲ ማህበረሰብ የሠብአዊና የፍትሕ ጥያቄ ሲቀርብ ግን እርሱ የእኔ ጒዳይ ነው ተዉት እያለ የሰው ልጆችን ከሰብዓዊነት ውጭ በመጨቆን በዚህ ዘመን የማይጠበቅ የጭቆናና የብዝበዛ ስርዓት በመሆን ቀጥሏል፤በየትኛውም የዓለም ሀገራት የማይፈፀም ግፍ ዛሬ በኢትዬጵያ ይፈፀማል።
የኢትዬጵያ ሕዝብ የሚያታግለው ስለአጣ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ያካበተው ርህሩሕነት፣ቸርነት፣ቻይነት፣ይቅር ባይነት፣በመቻቻል አብሮ በጋራ መኖርንና መስማማትን ይዞ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ ዛሬ ሕወሐት/ኢሕሐዴግ እነዚህን ጠቃሚ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶች ለመጣል እየሞከረ ይገኛል፤ይሁንና በሕዝቡ ላይ ከልክ ያለፈ ግፍ በመፈፀሙና እነዚህን ለአገሪቷም ሆነ ለመሪዎቿ የሚጠቅሙ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶችን ከሕዝቡ ላይ ለመሸርሸር በመሞከሩ ዛሬ ሕወሐት/ኢሕሐዴግን ለመጋፈጥ ብዙዎች ወደ ትግሉ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ከለየለት ጥፋቱ ለመመለስ ባለመፈለጉና የሕዝብን ትግስት እንደፈሪ በመቁጠሩ ዛሬ ውጥረቱ
በራሱ በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ላይ ነግሷል፤ ወደደም ጠላም ተወጥሯል፤ሕዝቡ በድፍረት በሠላማዊ ሠልፍ ብቻ ለሕወሐት/ኢሕሐዴግ ጥላቻዉን እየገለፀ ይገኛል፤ይህም በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ሠፈር ትልቅ ድንጋጤን በመፍጠሩ የዉጥረቱን መጠን ለመቀነስ የሚደረጒ ልዩልዩ ስብሰባዎችም ቢሆኑ ሌላ ተጨማሪ ድንጋጤን በገዢዎቻችን ሠፈር እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ የዲሞክራሲና የፍትህ ፅንሰ ሐሳቦች በፍፁም የማይገባዉና በ60ዎቹ የሶሻሊስት አስተሳሰቦች ተተብትቦ ፤በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ባለዉ ንቀት የተነሳና ይኸዉ አሮጌ አስተሳሰቡ ዓለም ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አብረዉ ሊጓዙ የሚችሉ ወጣቶችን ለመሰብሰብ ባለመቻሉ፣የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ባለመፈለጉና በዚሁ አሮጌ አስተሳሰቦችና በጥላቻ ፖለቲካ በተመረዙ ሰዎች እየተመራ በመሆኑ ዛሬ ውጥረቱ በራሱ በድርጅቱ ዉስጥ እየሰፋ መምጣቱን ከራሱ ከድርጅቱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ዛሬ ኢትዬጵያ ግልፅ ባልሆነ መልኩ በተደራጁ ማፍያዎች እንደምትመራ ኢትዬጵያን ብቻ ሳይሆኑ የአለም መሪዎች ጭምር እያወቁ የመጡ ይመስላል።
በቅርቡ እንኳን በዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ በጁን 20,2013 በኮንግረስ ማን የተከበሩ ስሚዝ ሰብሳቢነት በኢትዩጵያ ባለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ከመለስ በኋላ የምስክርነት ቃል መስማት በተከናወነበት ወቅት የተሰነዘሩት አስተየቶችና ለኢትዬጵያ መሪዎች ማነቆ የሚሆኑ ሕጐችን ለማውጣት ቃል መግባታቸዉን ስንመለከት አሜሪካ ከዚህ ስብሰባ በስተጀርባ በኢትዩጵያ ጉዳይ ላይ ያላትን ዕቅድ ለመተግበር መነሳቷን አልያም የሕወሐት/ኢሕሐዴግ መሪዎች አካሄድ እንዳላስደሰታቸው ያመለክታል።
ባለፈው ሰሞን የኢትዩጵያ የልማት ድጋፍ ስጪ አገሮች አምባሳደሮች የሰማያዊ ፖርቲ አመራርን ለማነጋገርና አንዳንድ መረጃ ለመለዋወጥ ማቀዳቸውና መተግበራቸው ከሕወሐት/ኢሕሐዴግ የይስሙላ ዴሞክራሲ ጋር ቅራኔ አንዳላቸውና በሕዝብ እንቅስቃሴም ዙሪያ የተለየ እይታ ይዘው መቅረባቸውን ፤እንዲሁም ለዘለቄታ ግንኙነታቸውና ጥቅሞቻቸው ሕዝብ ከጠላው ጋር መስራታቸው በታሪክ ሊያስጠይቃቸው እንደሚችል የገባቸውና ፤እነሱም ለውጥ ፈላጊ መሆናቸውን ማየት ይቻላል።
አውሮፓ ሕብረት የፖርላማ ተወካዬች በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለመነጋገር በኢትዩጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ብንመለከት ደግሞ «ኑና እዪ»  የተባሉ ይመስል ሕዝቡ ላይ ያለዉን ችግር እራሳቸው በቅርበት ያዩትና እራሳቸውን ጭምር ያሳዘናቸው መሆኑና ፤የኢትዩጵያ ችግር እምን ደረጃ እንደደረሰ ለመረዳት ችለዋል። እነዚህ የአውሮፓ ህብረት የፖርላማ አባላት ኢትዩጵያ በምን አይነት ሰዎች እንደምትመራ ለመረዳት እንደቻሉና የተለየ አግራሞት እንደፈጠረባቸዉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል ፤ ከዚህም የተነሳ ይመስላል የህብረቱ አባላት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ከስር እነዲለቀቁ ፣ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ፣የእምነትና የሀይማኖት ተቋማት መብትና ነፆነት እንዲከበር መግለጫ እስከማዉጣት የተገደዱት።
ይህ ብቻ አይደለም በሃገራችን በሁለቱ ትልልቅ የሐይማኖት ተቋማት አካባቢ ያለዉ « የፍትህ ያለህ » ጥያቄዎች በኢትዩጵያ መሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ባይነት ችግሩ እየተባባሰ ለመፍታት ወደሚቸግር አቅጣጫ እየመጡ መሆኑ የየዕለት ዜናዎች ሆነዋል።
ሌላው የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ባለስልጣናት በመላው ዓለም ከኢትዩጵያን ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የሚገጥማቸዉ ተቃዉሞ በሌሎች  አገሮች ህዝቦች የሌለ በመሆኑ ህወሃቶች ምን ያህል በአገራቸዉ ዜጎች ዘንድ የተኮንኑ ለመሆናቸዉና አመኔታ የማይጥልባቸው መሆኑ እየታወቀ መምጣቱና በኢትዩጵያ አስክፊዉ ስርአት መሪዎች አካባቢ ትልቅ ድንገጤን እየፈጠረ መምጣቱ የቅርብ ጊዜያት እዉነታዎች ናቸዉ።
በቅርብ ደግሞ በሶስቱ ዋናዋና በአገር ውስጥ የስላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች ማለትም በሰማያዊ ፓርቲ፣በአንድነትና በመድረክ ላይ እየደረሰ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ በህዝቡ ተቀባይነት ባይኖርዉም እንደለመደዉ ለጥቃት መዘጋጀቱንና በነዚህም ፓርቲዎች አባላተ ላይ እየደረሰ ያለዉ እስራትና ማዋከብ በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ፓርቲ ላይ ትልቅ ውጥረትና ድንጋጤ መፍጠሩን ያመለክታል።
ሌላው በተለያዩ ጊዜያት ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ለኤርትራ መንግስት የሚያቀርባችዉ በስጦታ የታጀቡ የንታረቅ ልምምጦች  ድንገት ሊነሳ የሚችል ጦርነት በስልጠናቸው ላይ የሚፈጥረዉ ችግር ትልቅ ፍርሃት እንደፈጠረባችውና ለስልጠናቸዉ ሲሉ የትኛውንም ነገር ለመስጠት መዘጋጀታቸዉን ያሳያል።
እነዚህ በገዢዉ ፓርቲ አካባቢ ያሉት ዉጥረቶች በስለላ መዋቅር ብዛት ፣ በስር ቤቶች ብዛት ፣ በወታደራዊ ትጥቅና ስልጠና ብዛት መፍትሄ  የማያገኙባቸዉ ዋናዋና ምክንያቶች ህዝቡ ክልክ ያለፈ ጭቆና ዉስጥ መዉደቁ ፣ግልጽ ዘር መድሎ መኖሩ፣ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና መዘፈቃቸዉና የገዢዉ ፓርቲ ንግድ ተቋማት የንግድ ብዝበዛና ሌሎችም ህዝቡን ስላስመረረዉ ትግሉ የማይቆም ትግል መሆኑን ሁሉም ኢትዮዽያዊ እየተረዳ ያለው ሀቅ መሆኑም ጭምር ነው።
በአለፉት ዓመታት በዝርፊያ ፣በዘር ማጥፋት ተግባር ፣ ህዝቡን በማሰርና በመግደል፣በዘረኝነት መድሎ፣ በከፍተኛ ሙስና ተግባርና በሌሎችም ሀገርንና ህዝብን ሊጎዱ በሚችሉ ተግባራት ላይ መሰማራቱ ሊቀጥል እንደማይችል ሁሉም የተረዳዉ ሀቅ ሆኗል ።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች የስቪክ ማህበራትና ሌሎች የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ አሁን ኢትዩጵያ ካለችበት ሁኔታ አንፃር  ኢትዩጵያን ከለየለት ጭቆና ለማላቀቅ በሚደርገዉ ትግል ይበልጥ መስባስብ ፣መመካከርና የመፍትሄ አቅጣጫን አስቀምጦ መንቀሳቀስ ጊዜዉ የሚጠይቀዉ ጉዳይ በመሆኑና የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ውጥረት በህዝቡና በሃገሪቷ ላይ ሌላ ተጨማሪ ችግር እንዳይፈጥር አስቀድሞ መከላከል ጠቃሚ ነው እላለሁ።
እግዚአብሔር ኢትዩጵያን ይባርክ!

በአቶ መለስ ልጅ ስም በኒዮርክ ባንክ አለ የተባለውን 5 ቢሊዮን ዶላር የሚያሳየው ቼክ ጉዳይ እንዲጣራ ለአሜሪካ መንግስት ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ


የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 21 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<…በግብጽ አዲሱን ሕዝባዊ አብዮት ያስነሱት ሻይ ቤት እንደ ቀልድ የመከሩ፤ ከኮምፒዩተር በስተቀር መሳሪያ የሌላቸው፤ በዕምነታቸው ሙስሊም የሆኑ የሙርሲ መራጮች ነበሩ። በአንድ ዓመት አገዛዙ የተማረሩ ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ሚሊዮኖችን አደባባይ አውጥተው እንዴት መንግስት ሊቀይሩ ቻሉ? …>>
የግብጽን አብዮት በአብነት ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር ቃኝተነዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)
<<…ሽማግሌዎቹ ለእኛ ያመጡት አዲስ ነገር የለም…>>አቶ ሞገስ ሽፈራው በቬጋስ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት አሽከርካሪዎች የሕግ ጉዳይ ኮሚቴ አባላት አንዱ
<<…ሃያ አንድ ዓመታት ያስቆጠረው የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ውስጥ ያስከተለው ጉዳትና የፈጠረው ቀውስ ሲፈተሽ (ወቅታዊ ትንታኔ)
<<…እዚህ ጋር ቁምልኝ አለኝ። አደጋ ያስከትላል አይቻልም አልኩት። በግድ ታክሲውን ሊያቆም ሞከረ።አልቻለም። ሳላስበው መታኝ። ራሴን ሳየው ደምቻለሁ። ተጎድቼ ነበር።…>>
በተሳፋሪ የተደበደበ ኢትዮጵያዊ የታክሲ አሽከርካሪ በቬጋስ በዐይኑ አካባቢ በጉዳት እስከመሰፋት ስለደረሰበት ድብደባ ከተናገረው(ሙሉውን ያዳምጡ)
ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን
ዜናዎቻችን
በአቶ መለስ ልጅ ስም በኒዮርክ ባንክ አለ የተባለውን 5 ቢሊዮን ዶላር የሚያሳየው ቼክ ጉዳይ እንዲጣራ ለአሜሪካ መንግስት ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምርጫ 97ቱ ሚሊዮኖች የወጡበት የሚያዚያ 30 ሰልፍ በተግባር እንዲደገም ጥሪ አቀረበ
ግብጽ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ እንድታቆም አስጠነቀቀች
ካይሮ ዛሬም በአመጽ እየተናጠች ነው
ጠበቃ ተማም የጸረ ሽብር ሕጉን ህገወጥነት በአንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ አስረዱ
የትራይቮን ማርቲን ገዳይ የሆነው ጆርጅ ዚመርማን ከሕግ ቢያመልጥ ከፈጣሪ ተጠያቂነት እንደማያመልጥ ከጉዳዩ ነጻ ካሉት ዳኞች አንዱዋ ተናገሩ
የሙስሊሙ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ የተሳካ እንደነበር ተገለጸ
በቬጋስ የሚገኙ ሙስሊሞች ትግሉን ደግፈው በጋራ ተሰባስበው የአቋም መግለጫ አወጡ

የአንድነት ከፍተኛ አመራር የህይወት ታሪክ እንዳይነበብ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ከለከሉ



  • digg
  • 38
     
    Share
የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ ወ/ሰንበት የቀብር ስነስርዓት ላይ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ የፈለገህይወት አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤ/ክ አስተዳደር ከለከለ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ወዳጅ በተገኘበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅሟል፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸው ላይ የህይወት ታሪካቸውን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለማንበብ ሲዘጋጁ የሳሪስ ፈለገ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪዎች ከልክለዋል፡፡
አስተዳዳሪዎቹ የሰጡት ምክንያት አቶ ግርማ የህይወት ታሪካቸውDSCN2285 እንዳይነበብ ተናዘዋል የሚል የሐሰት መረጃ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ ከመከልከል አልፈው የፖለቲካ ተሳትፏቸው የሌለበትን የህይወት ታሪክ እንዲነበብ አድርገዋል፡፡ በሁኔታው ቅር የተሰኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ይህንን ህገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ የአቶ ግርማ የህይወት ታሪክ ከቀብር ስነስርዓት በኋላ በዛው በቤተክርስቲያና አውደምህረት ላይ በአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ተነቧል፡፡DSCN2287    DSCN2288DSCN2289DSCN2332DSCN2301

Sunday, July 28, 2013

ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊው ፈላሻ ጠበቃውንና የጠበቃውን ሴት ልጅ ገደለ


ማከሰኞ ጠዋት በፍች ጉዳይ ምክንያት በጠበቃው ክርክር የልረካው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ ጠበቃውንና የጠበቃውን ሴት ልጅ ገደለ፡፡securityguard
እስራኤላዊው የፖሊስ ቃል አቀባይ እንደተናገረው ተጠርጣሪው በአካባቢው በሚገኝ ህንፃ የጥበቃ ስራ ይሰራ እነደነበርና ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት አካባቢ ግድያውን እንደፈጸመ ተናግሯል፡፡
ጌታጎን ታደሰ የተባለው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ የጥበቃ ሰራተኛ በፍች ሂደት ውስጥ እንደነበርና ሟች ጠበቃን ቀጠሮ ይከራከር እንደነበር የፖሊች ዘገባ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ግን በፍርድ ሂደቱ ያልረካ በመሆኑ ጠበቃው ጋር ሄዶ የከፈለውን ብር እንዲመልስለት ጠይቆት እንደነበርና ቀጥሎም በያዘው መሳሪያ ጠበቃውንና ሴት ልጁን ከቅርብ ርቀት ተኩሶ እንደገደላቸው ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊም ወንጀሉን እንደፈጸመ በፖሊስ እንደተያዘና እርስ በረሱ የተቃረነ ማስረጃ እንደሰጠ የተዘገበ ሲሆን በወንጀሉ ወቅት አእምሮው ትክክል እንደማያስብ ተናግሯል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊው ምንም አይነት የአእምሮ ህመም እንደሌለበትና የጥበቃ ስራውን ሲጀምር የተሰጠውን የአእምር,ሮ ጤንነት ፈተና አልፎ መሳሪያ እንደተሰጠው ተጠቅሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ዳኛው ሮብለት የአእምሮ ህመም ምርመራ እንዲያደርግና ለስምንት ተጨማሪ ቀናት እንዲቆይ ትዛዝ ሰጥተዋል፡፡  freedom4ethiopian
የ49 ዓመቱ ጌታጎን ታደሰ የ4 ልጆች አባትና በ2004 ዓ. ም. ከኢትየጵያ ወደ እስራኤል የመጣ ፈላሻ እንደሆነ መረጃዎቹ የጠቁማሉ፡፡
ማከሰኞና ባለፈው ግንቦት ወር ላይ በተፈጸመው ክስተት ምክንያት የእስራኤል ቁጥጥር ቢሮ በመሳሪያ አያያዝ ላይ የተሻሻለ ህግ እንደሚያስፈልግ ረቡእ እለት አስታውቋል፡፡ የሟች ጠበቃና የሴት ልጁ የቀብር ስነ-ስርዓትም በተመሳሳይ ቀን ሮብለት ተፈጽሟል
source Sodere .com

114 ኪሎ ሜትር የሐዲድ መስመር ለመዘርጋት ለባከነው 60 ሚሊዮን ዩሮ ተጠያቂው ማነው?

በአገራችን ለትራንስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ ሲሰጡ ከነበሩ አንጋፋና ታላላቅ ድርጅቶች መካከል የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት አንዱና በሁለት እህትማማቾች አገሮችና (በኢትዮጵያና በጂቡቲ) ሕዝቦች መካከል ዲፕሎማሲያዊ ትስስሩ የማይበጠስ የጋራ መገናኛ ድርጅት እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
ድርጅቱ ከዚህም ባሻገር ከአገራችን የሚወጡና ወደ አገራችን የሚገቡ ከፍተኛ ክብደት ያላቸውንና መጠነ ብዙ ለአገር ግንባታ የሚውሉ የፋብሪካ፣ የግብርና ወዘተ. ግባቶችን የሚያመላልስ ጠቃሚ የትራንስፖርት አካል ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የመሀልና የዳር አገር ሕዝቦችም የኢኮኖሚ ጥምረት እንዲኖራቸው ያገዘና በርካታ ቤተሰቦችም እንዲተዳደሩበት ያደረገ እናት ድርጅት ነበር፡፡
ይሁንና ይህ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ድርጅት በማርጀት፣ በጦርነት፣ በተፈጥሮና በአስተዳደራዊ ችግሮች ወዘተ. እንደቀድሞው ሊቀጥል ባለመቻሉ አንዳንድ ችግሮችን በተለይም በእርጅና የተበላሹ ሐዲዶችን (መስመሮች) መቀየር እንዲችል ከአውሮፓ ሕብረት (EU) የ60 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ ተሰጥቶት የ114 ኪሎ ሜትር መንገድ እድሳት እንዲደረግ ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር ከተባለ የጣሊያን ድርጅት ጋር ውል ተደርጐ ሥራው ከአምስት ዓመታት በፊት እንዲጀመር መደረጉ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ይህ የተባለው የኢጣሊያ ኩባንያ ከጅምሩ ለሥራው ብቁ እንዳልነበረ እየታወቀና በተለያዩ ጊዜያት ኃላፊነት ያለባቸው የምድር ባቡር የማኔጅመንት አባላት፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር ተወካይ፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ እንደዚሁም ኮንሰልታንት የነበረው ኢኔኮ የተባለው ስፔናዊ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጭምር ባልሳሳት በየጊዜው የተሠራውንና የተደረሰበትን ለመገምገም ድሬዳዋ እየተገናኙ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ሆኖም ጠብ ያለ ሥራ ሳይሠራና 30 ኪሎ ሜትር ያህል እንኳን ሐዲድ ሳይዘረጋ ጠያቂም ተጠያቂም ሳይኖር ድርጅቱ (ኮንስታ) ከ1/3ኛ በላይ የሆነ ገንዘብ ካባከነ በኋላ የተጀመረው ሥራ እንዲቆም ተደርጓል፡፡
የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ ምንም እንዳልተሠራና የመስመርና የድልድይ ሐዲዶች ተነስተው ለባሰ ኪሣራና ውድመት ድርጅቱ መዳረጉ እየታወቀ፣ ሕዝብና መንግሥትን ለማታለል መስመሩ እንደተሠራና እንዳለቀ ተቆጥሮ ባለፈው አምስት ወር ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ድል ያለ ድግስ ተደግሶ ምረቃ መደረጉ ነው፡፡ ለኮንስታም ድርጅት ሽልማት መስጠቱ እንደዚሁም በድርጅቱ ኃላፊዎችም የትራንስፖርት ሥራው ተጀምሮ በሳምንት አምስት ጊዜ ባቡር እየተመላለሰና ሥራው እንደተጀመረ መግለጫ መሰጠቱ አነጋጋሪ ነው፡፡
በያዝነው ወር ደግሞ የ114ቱ ኪሎ ሜትር 60 ሚሊዮን ዩሮና ለድግሱ ወጪ ብክነት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ሳይለይ፣ ከድሬዳዋ ጂቡቲ መስመር ለማስቀጠል የድርጅቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የሐዲድ መስመሩን ለመጠጋገን ዘመቻ ጀምረዋል (በቅርቡ አይሻ ላሠራውና ጐርፍ ወስዶት ተጠገነ የተባለውን 2,000,000 ብር ወጪ የሆነውን ሳይጨምር)፡፡ ሆኖም ግን ይሳካላቸው አይሳካላቸው ፈጣሪ የሚያውቀው ቢሆንም፣ ከ30 ዓመታት በላይ ድርጅቱን ሲመሩ የነበሩና ፈጽሞ ለኪሣራ የዳረጉ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ በሐዲድ ሥራ ላይ (በባቡር ቴክኖሎጂ) ምንም ዓይነት ዕውቀት የሌላቸውና በሙስና የተጨመላለቁ የማኔጅመንት አባላት፣ ትላንት ድርጅቱ አነስተኛ ቢሆንም ለባቡሮችና ለጋሪዎች እንደዚሁም ለመስመር ሥራው ሐዲዶችና መለዋወጫዎች እያሉት ማስተዳደር ያልቻሉ፣ በቂ ባለሙያ በሌለበትና ሥራውን ለቆ በሄደበት ሁኔታ ዛሬ ከዜሮ ተነስቶ ምንም ሳይኖር ከድሬዳዋ ጂቡቲ ባቡር እንዲቀጥል እናደርጋለን ብሎ በድፍረት መነሳሳት፣ አገርን ለከፍተኛ ወጪ ሕዝብን ደግሞ ለአደጋ የሚዳርግ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ መቀለድ ስለሆነ ሊታሰብበት እንደሚገባ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ፡፡
(ሜንታ ነኝ፣ ከድሬዳዋ)
************
የ15 ከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ወቅታዊ ሁኔታ
የ15 ከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና በአውሮፓ ኅብረት ብድርና ዕርዳታ በመካሄድ ላይ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ሦስት አካላት ያሉት ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 36.2 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡ ይህም 16.5 ሚሊዮን ዩሮ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በብድር፣ 16.5 ሚሊዮን ዩሮ ከአውሮፓ ኅብረት በዕርዳታ የተገኘ ሲሆን፣ የተቀረውን ማለትም 3.2 ሚሊዮን ዩሮ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ነው፡፡
ነገር ግን በጨረታ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋ በመናሩ ምክንያት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ 50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ እንደሚያስፈልግ ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን በ2010 በተደረገው የጨረታ ሒደት የግንባታ ጨረታው ኮንስታ ስፓ ይመራው ከነበረው የሦስት ድርጅቶች ጥምረት ወይም ሽርክና ማቲዮሊ ጆይንት ቬንቸር በመባል ይጠሩ ከነበሩ የኮንትራክተር ስብስቦች ጋር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ውል በመፈራረም፣ ግንባታው እ.ኤ.አ. ጥር 20 ቀን በ2011 በይፋ ተጀምሮ ነበር፡፡
ሆኖም ኮንትራክተሩ በገባው ውል መሠረት ሥራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠውን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች፣ ትዕዛዞችና ማስጠንቀቂያዎች ላይ ትኩረት ባለመሰጠቱ ከድርጅቱ ጋር የነበሩንን ውሎች አስመልክቶ ከአበዳሪ፣ ከለጋሽ ድርጅቶቹና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር መወሰድ የሚገባውን ዕርምጃ አስመልክቶ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ምክክሮች ከተደረጉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 12 ቀን 2013 ጀምሮ የግንባታ ውሉ እንዲቋረጥ ሆኗል፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አቋም መሠረት ይህ የውል መቋረጥ ቀደም ሲል መደረግ የነበረበት ቢሆንም፣ ከአውሮፓ ኅብረት የተገኘውን ዕርዳታ ላለማጣት ሲባል እንዲዘገይ ተደርጓል፡፡
ስለዚህ በቅርቡ የተከሰተው መቋረጥ የግንባታ ውሎቹ መቋረጥ ብቻ እንጂ ፕሮጀክቱ አለመቋረጡ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ወቅት ከሁለቱ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር ያሉንን የብድርና ዕርዳታ ስምምነቶች ለማራዘም ከመግባባት ተደርሶ ጉዳዩ በሒደት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሁለቱ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች በተደረገው ስምምነት መሠረት የተቀሩት ሥራዎችን ለማስጨረስ የጨረታ ሒደቱ እንዴት መሆን እንዳለበትና በምን መልኩ ሒደቱን ማሳጠር እንደሚቻል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተወያይቶ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
በመሆኑም በቅርቡ በተቋረጡት ኮንትራክቶች ያልተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች ለማስቆፈር ከአንድ ኢትዮጵያ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት የተፈጸመ ሲሆን፣ የቧንቧና መገጣጠሚያዎች ግዢን ለማከናወን የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የቧንቧና መገጣጠሚያዎች ግዢ ጨረታ በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ የተቀሩት የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዢና ተከላ የጨረታ ሰነዶች ዝግጅት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅና አየር ላይ እንደሚውል እናረጋግጣለን፡፡ በሌላ ወገን የፕሮጀክቱ አካል የሆነው የአቅም ግንባታ ሥራ ውል ተፈጽሞ በአሁኑ ወቅት በተመረጡ ስምንት ከተሞች ሥራው ተጀምሯል፡፡
(የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር)
የጥቂት ዳያስፖራዎችን ሕገወጥ ተግባር የሚመለከት ጥቆማ 
የኢትዮጵያ መንግሥት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጀምሮ አሁን በሥልጣን ላይ እስከሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ አገራችንን የበለፀገችና ለዜጎች ምቹ የሆነች አገር ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ እኛም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነን በተለያየ አጋጣሚ የሌላ አገር ዜግነት ያለን ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ባለን ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ ምቹ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደተግባር እንድንገባ ላደረጉትና እያደረጉት ላሉት በጎ ነገር ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
አሁን ግን ይህን የመንግሥትና የሕዝብ ጥሪ እንደ ልዩ አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ተቀባይነት በሌላቸው ሥራዎች ላይ በመሳተፍ አገር እየጎዱ፣ የመንግሥትን ገቢ እያሳጡ እንዲሁም የብዙውን አገር ወዳድ ዳያስፖራ ልፋት መና እያስቀሩ በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ዳያስፖራዎችን በቅርበት እየተመለከትን ነው፡፡
እነዚህ ዳያስፖራዎች ሕገወጥ ሥራዎችን በሕጋዊነት መጋረጃ በመጋረድ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከሚፈጽሙትም ሕገወጥ ተግባሮች መካከል በውጭ አገር ያፈሩትን ጥቂት ሀብት የተለያዩ ውስብስብ መንገዶችን በመጠቀም አራጣ በማበደር በአጭር ጊዜ ለመክበር የሚያደርጉት ጥረት አንዱ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በተደጋጋሚ ከአገር ሲወጡና ተመልሰው ሲመጡ የግል መገልገያዎች በማስመሰል የተለያዩ ቁሳቁሶችን (በተለይ ኮምፒውተሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና የተለያዩ መድኃኒቶችን) አስፈላጊውን የመንግሥት ቀረጥ ሳይከፍሉ ይዘው በመግባት፣ ንግድ ፍቃድ ሳያወጡም ሆነ አስፈላጊውን መንገድ ሳይከተሉ ለገበያ እያቀረቡ ሕጋዊ ነጋዴውን እየጎዱ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ፍቃድና መታወቂያ እንዲሰጥ ኃላፊነት የተሰጠው የመንግሥት አካል፣ አዲስ ፈቃድ ሲሰጥም ሆነ የነበረውን ሲያድስ አገር ውስጥ በምን ሥራ ላይ ለመሳተፍ እንዳሰቡና እየተሳተፉ እንደሚገኙ የማጣራት ሥራ ቢሠራ መልካም ነው፡፡ እንዲሁም የፍትሕ አካላትና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስፈላጊውን ክትትል ቢያደርጉ፣ ይህንን ሕገወጥ ተግባር ሥር ከመስደዱ በፊት ለመግታታት እንደሚቻል አምናለሁ፡፡
ከሁሉ ሁሉ በላይ ግን የአገራችን ልማት የሚናፍቀን ኢትዮጵያውያን ሆንን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ጥቂት ሕገወጦች ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ በቃችሁ በማለት ከመምከር ጀምሮ አስፈላጊውን ጥቆማ ለተገቢው አካል መስጠት ይገባል፡፡ ይህንንም ከማድረግ እነዚህ ግለሰቦች ከሕገወጥ ተግባራቸው ተገትተው ራሳቸውንም ሆነ አገርን በሚጠቅም ተግባር እንዲሳተፉ በማድረግ ለተነሳንለት ራዕይ የበኩላችንን ኃላፊነት እንድንወጣ እጠይቃለሁ፡፡
(የአገርን ጥቅም ከሚያስቀድሙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንዱ)
ethiopian reporter

ተጠርጣሪ ባለሥልጣናት ባለድርሻ የሆኑበት ‹‹ልማት በዕድገት›› የሚባል ድርጅት መገኘቱ ተጠቆመ


በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከሚገኙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በተጠረጠሩበት ወንጀል ታስረው የሚገኙት የትራንዚት ሠራተኛ በነበሩት አቶ ማሞ ኪሮስ ስም የተቋቋመና የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ባለድርሻ የሆኑበት ‹‹ልማት በዕድገት›› የሚባል ድርጅት መገኘቱን፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊ በነበሩት እነ አቶ ዳዊት ኢትዮጵያ የምርመራ መዝገብ በተፈቀደለት አሥር ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ሒደቶች ለችሎቱ እንዳስረዳው፣ አቶ ማሞ ኪሮስ የትራንዚት ሠራተኛ ሆነው ሳለ ‹‹ያለቀረጥ በነፃ ያስገቧቸው›› በሚል የተጠረጠሩ 22 ኮንቴይነሮች ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ተይዘዋል፡፡ ተጠርጣሪውና በሌላ ምርመራ መዝገብ የተካተቱ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባለድርሻ የሆኑበት፣ ‹‹ልማት በዕድገት›› በሚል ስያሜ አክሲዮን ማኅበር አቋቁመው መገኘቱን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡
አዲስ የተቋቋመውን ድርጅት አቶ ማሞ በሥራ አስኪያጅነት በሚመሩበት ጊዜ ‹‹ለድርጅቱ›› እየተባለ የተለያዩ ዕቃዎች ያለቀረጥ መግባታቸውን የሚያሳይ ፍንጭ ማግኘቱንም መርማሪ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ድርጅቱን የሚገመግምና የሚመረምር ቡድን አቋቁሞ እየሠራ መሆኑንም ቡድኑ አክሏል፡፡
የምስክሮችን ቃል መቀበሉን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ አዳማ፣ አዋሽና ሚሌ የተጓዘው መርማሪ ቡድንም በአጠቃላይ የ18 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን አስታውቋል፡፡
ሁሉም ተጠርጣሪዎች ያከማቹትን ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን በሚመለከት ባለሙያዎችን በማሰማራት እየሠራ መሆኑንም ቡድኑ ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ዳዊት ኢትዮጵያ፣ ማሞ አብዲ፣ አሸብር ተሰማ፣ ፍፁም ገብረ መድኅን፣ ማሞ ኪሮስ፣ አበበልኝ ተስፋዬና ኮነ ምህረቱ (በዋስ ተለቀዋል) ሲሆኑ፣ ሁሉም በግላቸውና በጠበቆቻቸው አማካይነት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸውና በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላው ፍርድ ቤቱ የተመለከተው በእነ አምባው ሰገድ አብርሃ (የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕግ ማስከበር ኃላፊ)፣ አቶ ተክለአብ ዘርአብሩክ፣ ያዴሳ ሚደቅሳ፣ እሸቱ ግረፍ፣ ጌታሁን ቱጂ፣ መላኩ ግርማ፣ አስፋው ሥዩም፣ ጌታነህ ግደይ፣ ዮሴፍ አዳዊ፣ በእግዚአብሔር አለበልና ዘለቀ ልየውን የምርመራ መዝገብ ነው፡፡
ኮሚሽኑ በተሰጠው አሥር የምርመራ ቀናት ለጠቋሚዎች ይከፈል የነበረን አበል፣ ቀረጥ ያልተከፈለባቸውና በሕገወጥ ጥቅም መመሳጠር የገቡ ዕቃዎችን፣ ታክስ ዝቅ የማድረግ ሥራን በሚመለከት ሰነድ መሰብሰቡንና ምስክሮችን መቀበሉን አስረድቷል፡፡
በሁሉም ተጠርጣሪዎች ማለትም በዕለቱ በቀረቡት 18 ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
እነ አምባው ሰገድ በራሳቸውና በጠበቆቻቸው አማካይነት የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን አሥር ቀናት በመፍቀድ ለሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ethiopian reporter

Tuesday, July 23, 2013

ሰበር ዜና፣ አዲስ አበባ ከተማ በግድግዳ ጽሁፎች (ግራፊቲ) ተሸፍና አደረች ድምፃችን ይሰማ

ሰኞ ሐምሌ 15/2005
እሁድ ምሽት ለሰኞ አጥቢያ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቦታዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄዎች በሚያንጸባርቁ ጥቅሶች ተጽፎባቸው አደሩ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ መንገዶች፣ የመንገድ አካፋዮች እና አጥሮች ላይ መንግስት ሕገ መንግሰቱን እንዲያከብርና በእምነት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቁ ጽሁፎች በትላልቅ ቁመት ለህዝብ በሚታይ መልኩ ተጽፈው የተገኙ ሲሆን ይህ በተጻፈባቸው ቦታዎችም ሰዎች ሁኔታውን በትኩረትና በግርምት ሲመለከቱ እንደነበር ታውቋል፡፡Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa1
በካዛንቺስ፣ በጦርሀይሎች በውንጌት አስኮ መንገድ እንዲሁም ገና በውል ባልታወቁ ቦታዎች ደምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ጥያቄያችን ይመለስ፣ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡብን የሚሉ ጽሁፎች ተጽፈው የታዩ ሲሆን በካባቢው የሚገኙ የወረዳ አስተዳደሮችም በተፈጠረው ነገር በመደናገጥ ጽሁፎቹን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡ የጎዳና እና የግድግዳ ጽሁፎች በአለም የታወቁ የመቃወሚያ ዘዴዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ መልእክቱን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎቹን አግባብ ባለው መልኩ ለመንግስት ሲያቀርብ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በዚህ እርምጃው በመቀጠልና ወደ ሌላ ሂደትም በመሸጋገር መንግስት ለሚወስዳቸው ማንኛውም እርምጃዎች እጅ እንደማይሰጥ በማሳየት ላይ የሚገኝ መሆኑን ይህ የዛሬ ክስተት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሙስሊሙን በአክራነትና አሸባሪነት በመፈረጅ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ ድምጹን ለማሰማትና መንግስት ምላሹን እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ አይነቱ ስልትም ሆነ በሌሎች ሰላማዊ መንገዶችና የመታገያ ስልቶች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሕጋዊ ጥቄዎች ብቻ የሚያንጸባርቁና ከትግሉ መንፈስ ያልወጡ መልእክቶች ሊተላለፉበት እንደሚችሉ ይታሰባል፡፡
አላሁ አክበር!
Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa2
Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa3

ሰበር ዜና: ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡ በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡

Sunday, July 21, 2013

አባቱን አያውቅም አያቱን ይጠይቃል!! ለጆሀር


ስለ ጆሀር ብዙ ነገር ተጽፎ በማህበራዊ ድረ ገጾችና የጡመራ ደሮች ተጽፎ አንብቢያለው፡፡ አንድ ወዳጄ ፌስ ቡክ ላይ ‹‹ስለ ጆሀር ምን አስተያዬት አለህ!›› አለኝ፡፡ እኔም ቪዲዮውን እንዳላየሁትና አስተያየት መስጠት እንደሚከብደኝ ነገርኩት፡፡ ይህ ወዳጄ ቪዲዮውን ‹‹ሸር›› አድርጎልኝ ደጋግሜ አዳመጥኩት፡፡
እኔ በጆሀር ንግግርም ፌስ ቡክ ላይ አስተያዬት በሚሰጡ ሰዎችም እኩል አዝኛለሁ፡፡ ጆሀር ለክርስቲያኖችና ኦሮሞ ላልሆኑ ዘውጌ ማህበረሰባት ያለውን ጥላቻ እኩል ገልጧል፡፡ ‹‹እኔ ባደግኩበት አካባቢ 99 በመቶ ሙስሊም በመሆኑ ማንም ሰው ደፍሮ አይነናገርም! በፌንጫ አንገቱን ነው የምንለው›› ይላል ለሌላ እምነት ተከታዮች ያለውን የበቀል ስሜት ሲገልጽ፡፡ ጎንደር ላይ ያለው ሙስሊም እንደሱ ‹‹በፌንጫ›› አለማለቱ ሁሉ ያናደደው ይመስላል፡፡
ወጣቱ ፖለቲከኛ ጆሀር ‹‹ኦሮሞና እስልምና ሀይማኖት›› አንድ ነው፡፡ የኦሮምን ህዝብ ትግል መደገፍ የእስልምናን ትግል መደገፍ አንድ አይነት ነው ብሎም ለመደምደም ይሞክራል፡፡ እስልምና በአቢሲኒያ ‹‹እንደ መጤ›› ይቆጠር ነበር፡፡ የአቢሲኒያ ነገስታት ለኦሮሞም ለእስልምናም የነበራቸውን አመለካከት ጥሩ አለመሆኑን በስፋት ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡ በተለይ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በመጣው በፖርተቹጋል ወታደሮች እስልምናን ለማስወጣት በነበረው እንቅስቃሴ የኦሮሞ የመከላከያ ሀይል እንዳሰቀረው አስረግጦ አብራርቷል፡፡
የጆሀር ንግግር ብዙ ህጸጾች እንዳሉበት ማንም ሰው የሚያምን ይመስለኛል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሀይማኖት ሙሉ በሙሉ እስልምና አለመሆኑን ጆሀር ይክደዋል ብዬ አላምንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በክርስትና ፣ በእስልምና እና በአካባቢው ባለ የቆየ እምነት (ዋቃ) ያምናል፡፡ ምንም እንኳ በመቶኛ ስሌት መገለጽ አሁን ባልችልም ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ አይደለም ሁለት ሶስተኛው እንኳ ሙስሊም ያልሆነን ማህበረሰብ የብሄርና የሀይማትን ትግል አንድ አድርጎ መመልከት ጤነኛ ነው ብየ አላምንም፡፡ አይደለም በኦሮሚያ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች እንኳ ሀይማኖትንና የብሄር ጭቆናን አንድ አድርጎ ለማየት መሞከር ‹‹ኋላ ቀር›› አስተሳሰብ የሚለው የሚለው ሀረግ የሚገልጸው አይደለም፡፡
ኦቦ ጆሀርን ተቀብሎ መድረኩን የተቆጣጠረው ስሙን የማለውቀው ሰው ከሰማንያው ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ 50 ሚሊዮኑ ሙስሊም አድርገው ሲናገሩ ‹‹ዳታው›› ከየት እንደተገኘ ባለውቅም እኔ ስለማውቃት ኢትዮጵያ እየተናገሩ እንደሆኑ አልገባህ ብሎኝ ነበር፡፡
ያም ሆነ ይህ በዚያ ቤት ላይ የነበረው ስብሰባ በጥላቻ የተሞላ እንደነበር ቪዲዮውን ያዬ ሁሉ ለመገንዘብ ጊዜ አይወስድበትም፡፡
ካንድ ወር በፊት አንዳንድ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት በካይሮ የኢትዮጵያን ግድብ ግንባታ ተቃውመው ሰልፍ ሲወጡ አቤ ቶክቾው ‹‹ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ተባልክ›› የሚል ጽሁፍ በድረ ገጹ አስነብቦ ነበር፡፡ እናም የነጆሀር ንግግር ሰላማዊ ሰልፍ ከወጡት ሰዎች አስተሳሰብ የተለየ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
እኔ ኦሮሞነትና እስልምና ይለያያሉ፣ አማርነትና ክርስትና ይለያያሉ፣ ትግሬነትና ክርስትና ይለያያሉ፣ አፋርነትና እስልምና ይለያያሉ፣ የትኛውንም ዘውግ ከየትኛው ከሀይማት ጋር ማመሳሰል አይቻልም፣ ይህ ማንም ምንም ቢል ሊያሳምነኝ የሚችል ሰው የለም፡፡
በተቃራኒው በግብጽ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን እና በጆሀርን ንግግር የሚቃወሙ አንዳንድ ጨዋት የጎደለው አስተያዬት የሚሰጡ ሰዎችንም ጽሁፍ ማንበብ ከኦቦው ንግግር እኩል ‹‹አፍራሽ›› አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሰዎች ቀላል አለመሆናቸውን ለማየት አስችሎኛል፡፡ ጆሀር አንድ ግለሰብ ነው፡፡ በምንም መልኩ የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮችና የኦሮሞ ማህበረሰባትን ሊወክል ፈጽሞ አይችልም፡፡ አይደለም ጆሀር ሁሉም የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ‹‹ኦሮሞን››፣ በተቃራኒው ሁሉም የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ‹‹እስልምናን›› መወከል አይችሉም፡፡
ስለዚህ በምን ስሌት እንደሆነ አላውቅም ከሌላ ዘውጌ ብሄረሰባት አካባቢ ያሉ ሰዎች በኦሮሞነትና በእስልምና ላይ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት የሚሰጡት፡፡ በርግጥ በሳል አስተያዬት የሚሰጡ የሉም ለማለት አይደለም፡፡ ግን ብዙዎቹ ጽንፍ ይዘው የተጻፉ መሆናቸው አሳዛኝ ነው፡፡
ወደ ርዕሴ ስመለስ ኦቦ ጆሀርን በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን አንኳር የታሪክ ፍሰት እንዲህ ላስታውሰው ፈለግኩ፡፡ ጆሀርን ብቻ አይደለም በጆሀር ፍልስፍና የተጠመቁ አጃቢዎቹን ጭምር እንጅ፡፡ በሀይማኖት እና በዘውግ የነበረውን የታሪክ ፍሰት ተጣጥሎ መመልከቱ አስፈላጊ መስሎ ስለታዬኝ ለየቅል እናየዋለን፡፡
1. ኢትዮጵያና ሀይማኖት
በኢትዮጵያ ታሪክ ከጥንት እስከ አለንት ዘመን ድረስ የነበሩ ገዢዎች ከጥቂቶች በቀር ክርስቲያኖች መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ይህ ታሪክ በመሆኑ እንጆሀርን ለማስደሰት ሲባል ከፊሉቹ ‹‹የእስልምና እምነት ተከታዮች ነበሩ›› አሊያም ‹‹እኩል በእኩል የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ነበሩ›› ብሎ ማስተካከል ከቶ የትኛው የታሪክ ምሁር ይቻለዋል!! የሚቻል ቢሆን ኖሮ ‹‹ለፍትሀዊነት›› ሲባል ማድረጉ ባልከፋ ነበር፡፡ በማይቻል ነገር ላይ ጊዜ ማጥፋቱ አስፈላጊ ባለመሆኑ ወደ ሌላው ጉዳይ ልለፍ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስትናን ካስተማራቸው ሰዎች አንዱ የኢትዮጵያዊቷን ንግስት ጃንደረባ ፊሊጶስ የተባለው ሀዋርያ አጠመቀና ወደ ሃገሩ ላከው (ሐዋ 8፡-)፡፡ ምንም እንኳ ይህ የሆነው በ34 ዓ.ም. እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ብሄራዊ ሀይማኖት የመሆን እድል አላገኘም ነበር፡፡
ኢትዮጵያ (የኢትዮጵያ ነገስታት) በ4ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ወይንም በ340 ዓ.ም. አካባቢ ክርስትናን ብሄራዊ ሀይማኖት አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ብዙዎቹ ነገስታቶቿ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነበሩ፡፡ አልፎ አልፎ ከኦርዶክስ ክርስትና እምነት ውጭ የነገሱ ወይም ወደ ሌላ ሀይማኖት የተቀየሩ ቢኖሩም በታሪክ በጥሩ መልኩ የሚወሱ አይደሉም (በጥሩ ላለመነሳታቸው ብዙ ምክንያት ሊኖር ይችላል፡፡ የታሪክ ጸሀፊዎቹ ክርስቲያን ስለሆኑ የሚያዩት ከራሳቸው ጥቅም አንጻር መሆኑ፣ በርግጥም ጥፋተኛ ስለሆኑ፣ … ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ችግር ማጥናት እና እውነተኛን ነገር ማሳወቅ/ ማወቅ የአንድ ጨዋ ሰው ግብሩ ነው)፡፡
በሰባተኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ነጃሽ የሚባል የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ እንደነገሰ ቢወራም ይህን የሚያጠናክር ከወሬ የዘለለ የታሪክ ድርሳን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ እርግጥ ነው በ622 ዓ.ም. አካባቢ መሀመድ እስልምናን ለአካባቢው ቋሪሾች ሲሰብክ ‹‹አይንህን ላፈር›› ሲሉት በዘመኑ ለነበረው ኢትዮጵያዊ ንጉስ ቤተሰቦቹን አደራ ሰጠው፡፡ ንጉሱንም እንግዳዎቹን ተቀብሎ አስገድዶ አላስጠመቃቸውም፡፡ ነጻነት ሰጣቸው፡፡ ምንም እንኳ ለስርወ መንግስቱ መዳከምና ጨርሶ መፈራረስ ብሎም የግዘቶቹ ስፋት ማነስ አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም፡፡ የአክሱም ስርዎ መንግስት ማክተሚያ ላይ በአስረኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በ980ቹ አካባቢ የነገሰችው የአይሁድ እምነት አራማጇ ዮዲት ስሟ በጥሩ ተነስቶ አያውቅም፡፡ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላለች፣ የታሪክ መዛግብትን አውድማለች፣ የብዙ ሰው ህይዎት ቀጥፋለች፤…. ብዙ ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሰርታ ከማለፏ የተነሳ ‹‹ዮዲት ጉዲት›› ተባለች (በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ጽንፈኛ አይሁዳዊ እምነት አራማጅ ሊህቅ አለመኖሩ ነው እንጅ ‹የአይሁዳዊነትን› ትግል ደግፉ ብሎ የሚነሳ ሰው ባልጠፋ ነበር)፡፡
በ16ኛው ክፍለ ዘመን የመባቻ አካባቢ አንድ ሃያል ጡንቻማ ሰው ከወደ ምስራቅ በኩል ብቅ አለ፡፡ የአዳሉ ንጉስ ሙሉ ስሙ ግራኝ አህመድ እብን ኢብራሂም አልጋዚ በአጭሩ ደግሞ ግራኝ አህመድ ይባላል፡፡ ከ1522-1540 ዓ.ም. ድረስ አጼውን እያሳደደ ከቆየ በኋላ ገደለው፡፡ ንጉሱም ባለቤታቸውን ‹‹ቀዳማዊት እመቤት›› ሰብለወንጌልን ጋለሞታ፣ ልጃቸውን ገላውዲዮስን ደግሞ እጓለማውታ አድረገው ወደማይቀረው አለም ሄዱ፡፡ አንበሳየም ከዮዲት ጉዲት በላይ ከአገር አገር እየዞረ አብያተ ክርስቲያናትን፣ የታሪክ መጽሀፍትን፣ ቅርሶችን… ወዘተ ከሚገበው በላይ አወደመ፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችን አሰለመ፤ አንሰልምም፣ ብለው የተቃወሙት ደግሞ ገድላቸው ያልተጻፉ ሰመዕታት ሆነው አለፉ፡፡ እልፍ አዕላፋት ነፍሳት አለቁ፡፡ (ከዚህ ላይ ጆሀር ከፖርቱጋል የመጡ ወታደሮች በእስልምና ላይ ከአገር ለማስዎጣት ያደረጉትን ጠቅሷል፡፡ ከኦቶማን ቱርክ የመጡትን ወታደሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ጉዳት ግን መግለጽ አልፈለገም፡፡) በ1543 ዓ.ም. አካባቢ ባይሞት ኖሮ ከዚህም የከፋ እልቂት ሊኖር ይቸል ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ግራኝ አህመድ ቅንጣት ታክል በጎ ምግባር ነበረው ያለ የታሪክ ጸሀፊ የለም:: ወይም ተጽፎ ቢሆንም በክርስቲያኖቹ ነገስታት እንዲጠፋ ተደርጎ ሊሆን ይችላል (የግራኝ አህመድ አስገድዶ ማስለም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ብዙዎቹ ነገስታት አስገድደው ክርስቲያን ያደርጉ ነበርና፡፡ ስለሆነም እሱ ያደረገው ብዙዎቹ ስልጣን ላይ ፊጥ ሲሉ የሚያደርጉትን በመሆኑና በዘመኑ በነበረው አስተሳሰብ መኮነን አለበት አልልም)፡፡
ታሪክ መልኩን እየቀያየረ ይደጋገማል፡፡ በ17ኛ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከ1608 – 1632 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው ንጉስ አጼ ሱስንዮስ ይባላል፡፡
የንጉሱ ዜና መዋልዕ እንደሚያስረዳው ንጉሱ ብዞ ጊዜያቸውን ያሳለፉት ከኦሮሞች ጋር በመሆኑ ከብሀረሰቡ በርካታ መልካም ሥብዕናንና ጦረኝነትን ተምረዋል፡፡ ንጉሱ በመጨረሻ የንግስና ዘመናቸው ካቶሊክን አምነው ተቀበሉ፡፡ ምን ይኸ ብቻ፤ ብሄራዊ ሀይማኖት እንዲሆን አወጁ፡፡ አይሆንም ያሉ መኳንንቶች ተቀሉ፤ ተሰየፉ፡፡ ህዝብ እርስ በእርሱ ተጨፋጨፈ፡፡ ኢትዮጵያችን እንደለመደችው በልጆቿ ደም ታጠበች፡፡ እማ ሙዝ/ ፍቅርተ ክርስቶስ የተባለች ጻድቅ ሰማዕት የሆነችው በዚህ ዘመን ነበር፡፡ /ገድለ ፍቅርተ ክርስቶስ መመልከት ይቻላል፡፡/ በመጨረሻ የንጉሱ ምላስ አርባ ክንድ ወደ ውጭ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ የንጉሱ ልጅ አቤቶ ፋሲል እንዲህ የሚል አዋጅ አወጀ፡፡
‹‹የሮም ሀይማት ይርከስ፣ የእስክንድር ሀይማኖት ትመለስ፣
ሱስንዮስ ይፍለስ፣ ፋሲል ይንገስ፡፡››
ይቀጥላል…፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እምየ ምኒልክ ይታመማሉ፡፡ በ1908 ዓ.ም አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ የሚተካ ወንድ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ የሸዋ መኳንንት ተጠበቡ፡፡ ከሞታቸው በኋላ የራስ ሚካኤልን ልጅ ወይም የቀድሞ የወሎውን ራስ አሊ ልጅ ልጅ ኢያሱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ልጅ ኢያሱ በአንድ በኩል ገና ሩጦ ያልጨረሰ ልጅ በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ በሀይማኖትና በብረሰባት ላይ ያለው አመለካከት ከሸዋ መኳንንት ፍላጎት ጋ ሊገጥም አልቻለም፡፡ ልጅ ኢያሱ ከክርስቲያኑም ከእስላሙም፣ ከአማራውም፣ ከኦሮሞውም፣ ከሶማሌውም ‹‹የሴት ወዳጅ›› እየያዘ በጋብቻ መልክ አንድነትን ለመፍጠር ያቀደው ሳይሳካ በነገሰ በሶስተኛ አመቱ በሌለበት ከዙፋኑ ተነሳ፡፡
2. ኢትዮጵያዊ ብሄረሰቦች
ኢትዮጵያችን ብዙ ቋንቋ ተናጋሪና ብዙ ባህል ያላቸውን ህዝቦች የያዘች አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ለልማቷም ለኋላ ቀርነቷም ሁሉም እኩል ሀላፊነት ይሸከማሉ ባይ ነኝ፡፡ አንዱ ሲያቀና ሌላው ሲያበላሽ፣ አሊያም ዝም ብሎ ሲመለከት፣ አንዱ አንዱን ሲያጠቃ የኖሩ ህዝቦችን የያዘች ሀገር ናት፡፡
አንዱ ብሄረሰብ ከየመን መጣ ሌላው ከደቡብ ምስራቅ አፍሪካ ጫፍ መጣ፣ አንዱ ቀድሞ ገባ ሌላው ዘግይቶ መጣ ለኢትዮጵያ ሁላችንም ልጆች ነን፡፡ ጆሀር እንደሚለው አንዱ ‹‹ማንነቱን›› በግዴታ የተቀበለው አሊያም ሌላው ደግሞ ‹‹ሰጪ እና ነሽ›› ሰዎች አይደለንም፡፡ መጋጨቱ፣ መፋቀሩ እና መናናቁ የታሪካችን አካል ሆኖ አልፏል፡፡ ግን አሁን ተማርን ያልን ሰዎች የበፊት ክፍተቶችን አርመን ወደ ፊት መጓዝ መቻል አለብን፡፡
ለምሳሌ በታሪክ የነበሩ እንዲህ አይነት ችግሮች አንኳር አንኳር የምንላቸውን ማየት እንችላለን፡፡ በሰለሞናዊውና በአገው ስርወ መንግስታት በነበረው ሽኩቻ ሰለሞናዊውን ስርዎ መንግስት አንኮታኩተው አገዎች የራሳቸውን መንግስት በ11/12ኛው ክፍለ ዘመን ዛግዌ ስርዎ መንግስት መሰረቱ እና ስልጣናቸውን በ1270 አካባቢ ፈጽመው እስኪያጡት ድረስ ተጠቀሙበት፡፡ በጣም ድንቅ የተባለው ‹‹የላሊበላ ኪነ ህንጻ ጥበብ›› የታየውም በዚሁ ዘመን ነበር፡፡ ምን አልባትም ንግስና ወደ አገዎች ባይመጣ ኖሮ ይህን የኪነ ህንጻ ጥበብ ላናውቅ እንችል ሁሉ ይሆን ነበር፡፡
በ15 /16ኛው ክፍለ ዘመን በነበረ የኦሮሞዎች የመስፋፍት እንቅስቃሴ ከሴሞቹ ጋር በነበረ ግጭት ብዙ ነገር እንደወደመ ግልጽ ነው፡፡ አማራዎቹ ይዘውት የነበረውን ለም መሬት በኦሮሞች በመነጠቅ ተራራ ላይ ብቻ እንዲወሰኑ ተገደዱ፡፡ በዚህ በኩል ከየትኛውም ብሄረሰብ የተሸለ ኦሮሞዎች ግዛታቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለመስፋፋት ቻሉ፡፡ ለዚህም ምስክር የሚሆኑ ብዙዎቹ ቦታዎች ቀድሞ የነበራቸውን ስያሜ በመተው ኦሮምኛ ስም ኖራቸው (ልክ አሁን ብዙዎቹ ከተሞች አማርኛ ስም አላቸው ተብሎ ወደ ኦሮምኛነት እንደተቀየሩት ሁሉ)፡፡ በተለይ ከአጼ ልብነ ድንግል እስከ አጼ ሱስንዮስ ድረስ በነበረው ጊዜ በነበረው የግዛት መስፋፋት ኦሮሞዎች እደለኞች ነበሩ፡፡ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ትግራይ ድረስ ገብተው ጥቃት ይፈጽሙ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ምንም እንኳ ድል አንዴ ላንዱ ሌላ ጊዜ ለሌላው ቢሆንም የነበረው የእርስ በእርስ ትርምስ ቀላል አልነበረም፡፡
ከዘመነ መሳፍንት በኋላ በሰሜን በኩል ያሉ ነገስታት ቀድመው መንቃታቸው ምን አልባትም በሌላው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ጠቅሟቸዋል፡፡ በአጼ ቴዎድሮስ የተጀመረው ሀገር የማቅናት ዘመቻ በአጼ ሚኒሊክ እስኪደመደም ድረስ የደረሰ ችግር አልነበረም ማለት አይቻልም፡፡ ግን ቀደም ብሎ ከነበረው ችግር የባሰ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ ቢናቆሩም በአገር አንድነት ላይ ያላቸው አቋም ግን የሚያስደንቅ ሆኖ ለረጅም ዘመናት ዘልቋል፡፡ የውጭ ሀይል አገር በወረረ ጊዜ ሁሉም እኩል ይፋለማሉ፡፡ በቅርቭ ጊዜ ያነበብኩት ‹‹የሀበሻ ጀብዱ›› የሚል በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የታተመና ከአውሮፓዊ ጸሀፊ የተተረጎመ መጽሀፍ ‹‹ኦሮሞዎቹንና አማራዎቹን›› አገር ወዳድ አርበኞች አድርጎ ስሏቸዋል፡፡ በተለይ አንድ ‹‹አቢቹ›› የተባለን ብላቴና ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወኔ በመደነቅ ነበር የገለጸው፡፡ ጆሀር የዚህን ልጅ ኢትዮጵያዊነት በምን መልኩ ሊያጣፋው እንደፈለገ አልገባኝም፡፡ አቤ ቶኪቻው ‹‹ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ተባልክ›› ያለው ወዶ አይደለም፡፡
ጆሀር ሞሀመድ እንበልና ሀሳቡ ቢሳካ እሱ አቢሲኒያ እያለ የሚጠራቸው ‹‹አማራዎች››ም ከሌላው ብሄረሰብ የበለጠ አይጎዱም፡፡ አብረው በመሆናቸውም የበለጠ አይጠቀሙም፡፡ ክርስቲያኖቹም በተመሳሳይ፡፡
እንደያው በመጨረሻ ግን ኦቦ ጆሀር በክርስቲያንና ኦርሞ ባልሆኑ ህዝቦች ላያ ያለው ጥላቻ ፈር የለቀቀ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ጥላቻቸው ከመጠን የዘለለ ሲሆን ወደ በቀል ይገባሉ፡፡ በቀሉ ደግሞ መደበቅ አይችልም፡፡ ኦቦ ጆሀር በ1984 ዓ.ም. በደኖ ላይ በነሌንጮ ለታ እና በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር የተገደሉ፣ በ1992/93 ወለጋ ጊዳ ኪላሞ ላይ ወደ እሳት የተጣሉትን ህጻናትን፣ በ1999 በጅማ በሻሻ የተሰ ክርስቲያኖችን፣ በቅርቡ ደግሞ በቢኒሻንጉል የተፈናቀሉ አማራዎችን አስብና አንድም የበቀል ስሜትህን አርከሰው አሊያም አንተ እንደፈለግከው፡፡
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር፡፡
ሰላም
በሙሉቀን ተስፋው 

ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል

ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል

የ10/90፤ 20/80 እና 40/60 ችብቸባው ቀጥሏል
jemo


አጠገብ ያሉ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ እንዲለቁ ተነገራቸው
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ለማድረግ ስምምነት ሊያደርግ ነው
በግዙፉ የጀሞ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች መንደር ውስጥ በአንድ በኩል በመስመጥ ላይ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሕንፃ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሕንፃው እንዲለቁ ተነገራቸው፡፡
በሁለቱ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሕንፃዎቹ እንዲለቁ የተጠየቁት በክፍለ ከተማው የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት አማካይነት መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የውሳኔው መነሻ ወደ አንድ ጐን በማዘንበል ላይ የሚገኘው ሕንፃ አጠገብ ያሉት ሁለት ሕንፃዎች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው በሚል ቢሆንም፣ በሕንፃዎቹ ላይ በዓይን የሚታይ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ሕንፃዎች ተመሳሳይ መሰነጣጠቅ በውስጥ አካላቸው ቢኖርም፣ መሰነጣጠቁ መቼ እንደተፈጠረ በእርግጠኝነት መናገር የሕንፃዎቹ ነዋሪዎች አይችሉም፡፡ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጡ የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሣ ወንድሙ ተጠይቀው፣ ስለተጠቀሱት ሕንፃ ነዋሪዎች የሰሙት ነገር እንደሌለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ነዋሪዎቹ በክፍለ ከተማው እንዲለቁና ተለዋጭ መኖሪያ ቤት እንዲወስዱ እንደተነገራቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
ችግር በታየበት ሕንፃ ላይ ይኖሩ የነበሩ ሁሉም ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት  ተለዋጭ ቤት እንደተሰጣቸው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በሕንፃው ላይ የተፈጠረው ችግር እንዲጠና በዚህ ሳምንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል እንደሚፈረም ያስረዱት አቶ ካሣ፣ ጥናቱ የጂኦ ቴክኒካል፣ የኮንትራክሽንና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን እንደሚያካትት አረጋግጠዋል፡፡
ጥናቱ ችግር ባለበት አንድ ሕንፃ ላይ ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በጠቅላላ የጋራ መንደሩ ላይ እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡ (ሪፖርተር)

መድረክ በመቀሌ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው ወጣት የሆኑ የመቀሌ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ስብሰባ የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ ጥላሁን እንደሻው፣ በአቶ ገብሩ አስራትና በአቶ ብርሀኑ በርኸ የተመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ስብሰባውን ስኬታማ አድርገውታል፡፡
በተሰብሳቢዎቹ በትግራይ ክልል የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር፣የሙስናና የግብር አሰባሰብ ችግሮችን በመንቀስ በመንግስት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ማንፀባረቃቸውንም አቶ ክብሮም አስረድተዋል፡፡ “መድረክ ላይ የነበሩት ተናጋሪዎች ሞቅ ባለ ጭብጨባ ታግዘው ተናግረዋል” ያሉት አቶ ክብሮም ስብሰባውን ለማደናቀፍ በአዳራሹ ውስጥና ውጪ በተደራጀ ሁኔታ ተሰብስበው የነበሩት ከየቀበሌው የተውጣጡ ካድሬዎች የተሰብሳቢው ሁኔታ አስደንድጧቸው እንደተበተኑም ተናግረዋል፡፡ በትላንትናው እለት የመኪና ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ ሁለት የአረና ትግራይና አንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መቀሌ ውስጥ ከነመኪናቸው በህገወጥ መንገድ ታስረው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ማናቸው? (ዐይናለም ግዛው ፡- ከኢየሩሳሌም)

አቡነ ማትያስ (አባ ተክለማርያም አስራት) 

H E Abune Matiyas
H E Abune Matiyas
ማሳሰቢያ፦ ይህ ጽሑፍ በመጀመሪያ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ለሚገኘው የነፃነት ለኢትዮጵያ ራድዮ የተላከው በእኔ ሥም ቢሆንም፣ በኀብረት ያዘጋጀነው ግን ጉዳዩ የከነከነንና ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን ምዕመናን(ት) ነን፤ ስለሆነም፣ ይህ ዘገባ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ፣ በታላቋ ብሪታንያ፣ በጀርመን፤ በእሥራኤል፣ በስዊትዘርላንድና በዩ. ኤስ. አሜሪካ ከሚገኙ የመረጃ ምንጮች ጋር በመተባበር ነው፡፡ በዘገባው ውስጥ የተካተቱት ጉዳዮች ሁሉ በአዲስ አበባዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በደህንነት ጥበቃው መ/ቤትና በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት፣ እንደዚሁም ደግሞ ቀደም ብለው በተጠቀሱት ስድስት ሀገሮች ውስጥ ከሚኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በተጨማሪ፣ በኢየሩሳሌሙ የመንበረ ጳጳስ ግቢ ቤተ መዘክርና በቆንስላው ጽ/ቤት በሥርዓት ተመዝግበው የተቀመጡ ናቸው፤ በኢየሩሳለሙ የመንበረ ጳጳስ ግቢ የነበረውን ማስረጃ ለማጥፋት አቡነ ማትያስ ዕድል ተሰጥቷቸው ነበር ቢባል እንኳን፣ በለሎቹ ዘንድ ያሉትን ሊደርሱባቸው ካለመቻላቸውም በላይ በህይወት ያሉ የቃል ምሥክሮችም ጥቂት አለመሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
ethioforem

የፀረ ሙስና ትግሉን ለመቀልበስ ያደፈጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መኖራቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡


አዲስ አበባ ላይ የተንሰራፋው ሙስና ለብዙዎች አሳሳቢ ሆኗል
መንግሥት ሙስናን እየተዋጋ የሚያስመስሉ ምልክቶች ቢስተዋሉም፣ የፀረ ሙስና ትግሉን ለመቀልበስ ያደፈጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መኖራቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙሰኞችን በተመለከተ ሲናገሩ፣ ‹‹ወይ እነሱ ያሸንፋሉ ወይ እኛ እናሸንፋለን፤›› ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን መንግሥት ሙስናን ለመታገል ደፋ ቀና የሚለውን ያህል በመንግሥት ጉያ ሥር ተሸጉጠው የሙስና ትግሉን በመቀልበስና የሚገኘውን አይስክሬም ለመላስ የቆረጡ እንዳሉ እየታየ መሆኑን የሚገልጹ አሉ፡፡
በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ሽኩቻ ወይም ትግል በማን አሸናፊነት እንደሚቋጭ ባይታወቅም አሸናፊና ተሸናፊ የግድ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እየጨሰ ከሚገኘው የፀረ ሙስና ትግል ባሻገር፣ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ጉዳዮችን ጥቂት ዓመታት ወደኋላ መለስ ተብሎ ቢመረመርና አሁን ካለበት ደረጃ ጋር ቢመዘን የጉዳዩን አሳሳቢነት መረዳት ያስችላል በማለት የሚገልጹ አሉ፡፡
የቀድሞወ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ አስተዳደር ሥልጣኑን ከእሳት አጥፊው ባለአደራ አስተዳደር ሲረከቡ ወደ ከተማው ይዘው ከመጧቸው ቁም ነገሮች መካከል መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሙስናን መታገልና መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ተግባራዊ ማድረግ ይገኙበታል፡፡
በተለይ ከገቢ አሰባሰብና ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ በርካታ የሙስና ተግባሮች እንደነበሩ በመታመኑ፣ በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ጠንከር ያለ ግምገማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ግምገማዎች በርካታ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በሙስና መዘፈቃቸውና በርካታ ገንዘብ መመዝበሩ በተካሄደው ድርጅታዊና መንግሥታዊ ግምገማ ተረጋግጧል፡፡
የግምገማው ውጤት ለፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተመራ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ በደረሰው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ምርመራ በጀመረበት ወቅት ግን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፀረ ሙስና ኮሚሽን በጻፈው ደብደቤ የተፈጠረው ችግር የከተማው ነው በሚል ምክንያት ኮሚሽኑ ምርመራውን እንዲያቆም ጠይቋል፡፡
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የአስተዳደሩና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለሙያዎች ሁኔታውን አሳፋሪ ሲሉ ይገልጹታል፡፡ ምክንያቱም ያጠፋ መጠየቅ አለበት፡፡ የተመዘበረ የመንግሥት ገንዘብም ሊመለስ ይገባዋል ሲሉ እነዚህ ባለሙያዎች ምክንያታቸውን ገልጸው፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከእንግዲህ ደብዳቤ መጻፍ እንደሌለበትና ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ምርመራውን ሊያቆም እንደማይገባ አስረግጠው መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡
በግምገማ ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠባቸውና ማጥፋታቸውን በግልጽ ያመኑ የሙስና ተጠርጣሪዎች  ግን ክስ አልተመሠረተባቸውም፡፡ ተመዝብሯል የተባለውም የመንግሥት ሀብት ተመላሽ አልተደረገም፡፡ በዚህ ምክንያት የተበደሉ ነዋሪዎችም እንዲካሱ አለመደረጉ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ብዙዎችን የሚያስገርመውና እያስገረመ የሚገኘው እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጠያቂ አለመሆናቸው ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁኑም በአዳዲስ ሹመቶች መንበሽበሻቸው ነው፡፡
ከአሥሩም ክፍላተ ከተሞች በሙስና ተግባር ውስጥ ተሰማርተዋል ተብሎ ነጥብ የተያዘባቸው ሹማምንት ከነበሩበት ክፍለ ከተማው ወደሌላ ክፍለ ከተማ ተቀይረው ተሹመዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በክፍላተ ከተሞች በሚገኙ የገቢ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ‹‹ሙሰኞች›› እንዳሉ ይነገራል፡፡
እነዚህ ‹‹ሙሰኞች›› ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ፍሬ ግብር በመቀነስ ሊከፈል የሚገባውን የመንግሥት ግብር የሚያሳንሱ፣ ማሳነስ ብቻም ሳይሆን ጭራሹኑ ሊገባ ይገባው የነበረ ገንዘብ ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት እንዳይገባ ዘብ የቆሙ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
እነዚህን ያጋለጡ ሠራተኞች ግን በየጊዜው ተፅዕኖ እየተደረገባቸው ጭራሹኑ በፍርኃት ካባ ተሸፍነው እንዲኖሩ እየተደረገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ ይህንን ሕገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ባላቸው ጠንካራ ኔትወርክ ምክንያት ለአዳዲስ ሹመቶች ሲታጩና ሲሾሙ ይስተዋላል፡፡
በሌላ በኩልም ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማዕከል ደረጃ በተካሄደው ግምገማ ከአሥር በላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሙስናና በኔትወርክ ተገምግመው ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ሐሳብ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከዛሬ ነገ ዕርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ ባለሥልጣናቱ ባሉበት ፀንተዋል፤ ወይም አዲስ ሹመት አግኝተዋል፡፡ በወቅቱ እነዚህ ባለሥልጣናት ሲገመገሙ በሙስና መዘፈቃቸውና በቡድንተኝነት (ኔትወርክ) ያልተገቡ ተግባራትን ይፈጽማሉ በሚል ምክንያት እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል፡፡
አስገራሚው ጉዳይ በአዲስ አበባ አዲስ ምርጫ ተካሄዶ አዲሱ ካቢኔ ሥልጣኑን ይይዛል ቢባልም፣ ወደከተማው የመጡት ከንቲባው ብቻ ናቸው፡፡ አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ነባሩን ካቢኔ ይዘው ማዝገማቸውን ቀጥለዋል፡፡
የቀድሞው የከተማው አስተዳደር በሚፈለገው ስፋትና ጥልቀት ባይሆንም የልማት ሥራዎችን መሥራቱ እርግጥ መሆኑን ብዙዎችን ያስማማል፡፡ በመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ በቤቶች ልማት፣ በመንገድ ልማት ዘርፎች የሚጨበጥ ሥራ ሠርቷል፡፡ ነገር ግን መልካም አስተዳደርን በማስፈንና ሙስናን በመዋጋት አገልጋይ ሲቪል ሰርቪስ ከመፍጠር አኳያ ብዙ እንደሚቀረው ብዙዎች ያምናሉ፡፡
የቀድሞው አስተዳደር መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና አገልጋይ ሲቪል ሰርቪስ በመፍጠር በኩል ፍላጎቱ ነበረው ቢባልም በአቅም ውሱንነት ባያሳካውም፣ ሙስናን በመታገል በኩል ግን የተነሳሽነት ችግር እንዳለበት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአስተዳደሩ ነባር ሠራተኞች ይናገራሉ፡፡
ኅብረተሰቡ ይህንን ችግር በመፍታት በኩል ኢሕአዴግ ቆራጥ መሆኑን በተደጋጋሚ በመግለጹ ምክንያት በአዲሱ አስተዳደር ላይ ተስፋ ቢጥሉም፣ አዲሱ አስተዳደር ከከንቲባው በስተቀር ነባሩን ካቢኔ ይዞ መቀጠሉ በተጣለው ተስፋ ላይ ደመና አጥልቷል፡፡ ምክንያቱም የሠራተኞችና የነዋሪዎች እንቀፋት የሆኑ ባለሥልጣናት ላይ ዕርምጃ ተወስዶ ሥርዓት የሰፈነበት ቢሮክራሲ ይኖራል የሚል እምነት ተጥሎ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁሉም ነገር ተዳፍኖ ምንም እንዳልተፈጠረ ተደርጎ ጉዞ ቢቀጥልም፣ ጉዳዩ ብዙዎችን ያስከፋ በመሆኑ መንግሥት የጽሞና ጊዜ ወስዶ ራሱን ሊፈትሽ እንደሚገባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ያስጠነቅቃሉ፡፡
ethiopian reporter