Thursday, July 11, 2013

«ዉጡ! ፤ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳተፉ» – እስክንድር ነጋ !

July 11, 2013
eskinder_Nega.Lennart_Kjorl ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም
አቶ በትረ ያእቆብ በቃሊት አቶ አንዱዋለም አራጌን እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በጎበኙበት ወቅት የሚከተለዉን መልእክት ከእስክንድር ነጋ ይዘው መጥተዋል። ተላናት ቅኝ የነበሩየአፍሪካ አገሮች በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት የትናየት እንደደረሱ የጠቆሙት አቶ እስክንድር «ትናንት የአፍሪካ መሪ እንዳልነበርን፣ ዛሬ ጭራ ሆነናል» ሲሉ በኢትዮጵያ ያለዉ የሕዝብንመብት የሚረግተ፣ አምባገናዊ ስር;አት መኖር ብሄራዊ ዉርደት እንደሆነም ገልሰዋል።
አቶ እስክንድር የአንድነት ፓርቲና ሌሎች እየመሩት ያለዉን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀለዉ ጥሪ አቅርበዋል። «ሁሉምኢትዮጵያዊ ጊዜና ቦታ ሳይገድበዉ በአንድነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል» የሚል አገርወድድነት የተሞላበት መል እክስት አስተላልፈዋል።
«የጠባቂዎችን ግልምጫና ሀይለ ቃል ተቋቁሞ በዚያ ዉጥረት በበዛበት ሁኔታ እንዲህ ሲል ነበር እስክንድር ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ለዲያስፖራዉ መልዕክቴንአስተላልፉልኝ ያለዉ» ሲኡ አቶ በትረ የእስክንድርን መልእክት እንደሚከተለው አቅርበዉታል።
“አገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ አጣብቂኝ ዉስጥ ትገኛለች ፤ እንደ አገር በመቀጠልና ባለመቀጠል አጣብቂኝ ዉስጥ፡፡ ይህ ደግሞ የህልዉና ጉዳይ ነዉ፡፡ በተጨማሪም እኛ ዜጎቿም በጭቆናፍዳችንን እያየን እንገኛለን፡፡ ትናንት በአዉሮፓዉያን ተጠፍጥፈዉ የተፈጠሩ እንዲሁም እኛ ያዋለድናቸዉ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ዲሞክራሲን ሲጎናፀፉ እኛ እያደር ወደ ኋላ እያዘገምንእንገኛልን፡፡ ትናንት የአፍሪካ መሪ እንዳልነበርን ዛሬ ጭራ ሆነናል ፤ ይህ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ፡፡”
“ስለሆነም ይህንን ችግር ከስሩ ለመቅረፍ የግድ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አሁን በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችመሪነት የተጀመረዉ የትግል እንቅስቃሴ ይበል የሚያስብልና የሚያበረታታ ነዉ፡፡ ትግሉ በዚሁ ተጠናክሮ ከቀጠለ እንዲሁም የሁላችን ተሳትፎ ከታከለበት ያለምንም ጥርጥር ወደ ነፃነትጎዳና ያደርሰናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጊዜና ቦታ ሳገድበዉ በአንድነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል፡፡”
“አትፍሩ! የአንባገነኖችን ዛቻ አትቀበሉ! ፍርሐት የአንባገነኖች ዋንኛ የአፈና መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ከልባችሁ አዉጡት፡፡ መቁሰል ፣ መታሰር እና መንገላታት ቢኖርም ይህየምንከፍለዉ መስዋትነት አገር አልባ ከመሆን ያድነናል ፤ የተሻለች አገር ለመገንባት ይረዳናል፡፡ ስለዚህ ዉጡ! ፤ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳተፉ፡፡”
እስክንድር አያይዞም ለዲያስፖራዉ እንዲህ አለ፡- “ዲያስፖራዉ ለሀገሩ ያለዉን ቀናኢነት የሚያሳይበት አጋጣሚ ይህ ነዉ፡፡ ለህዝቡ ያለዉን ፍቅርና ወገንተኝነት የሚገልፅበት መንገድነዉ፡፡ ይህንን በመረዳት አገር ወዳድ ከአገር ዉጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጠቅላላ በሚካሄዱ የተቃዉሞ ሰልፎች ላይ በተለይም አዲስ አበባ ላይ በሚካሄደዉ በአካል በመገኘትተሳታፊ ሁኑ፡፡”
EMF

No comments:

Post a Comment