
እንኳንስ ሌላው ቀርቶ፤ አዲስ አበባ ስታድየም የከተማው ደርቢ እግር ኳስ ጨዋታ ሲኖር የቡና ልጆች ሚስማር የሳንጃው ልጆች ደግሞ ዳፍ ነው የሚገቡት፡፡ ጥላ ፎቁንም ግራ እና ቀኝ ብለው ይካፈሉታል፡፡
ይህንን የሚያደርጉት ሁለቱም ቡድኖቻቸው በአንድ ሜዳ ስለሚጫወቱ ማዶ ለማዶ ሆነው መሀል ላይ የሚጫወተውን ቡድናቸውን ለማበረታታት ነው፡፡ እንጂ ለብሽሽቅ ብለው አይቀጣጠሩም… ኳስ ጨዋታ በሌለበት እስቲ እናንተም ውጡ እኛም እንውጣ እና እናደበላልቀው ብለው ሲጠራሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡
ነሀሴ 26 በመስቀል አደባባይ ሁለት ሰልፎች ተጠርተዋል፡፡ አንደኛው ሰማያዊ ፓርቲ ከሶስት ወር በፊት ላደረገው ሰልፍ ምላሽ ካላገኘሁ እመለስበታለሁ ብሎ ሲዘጋጅበት የከረመው ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ድንገት ከየት መጣ ከየት ሳንለው የተከሰተው የሀይማኖት ተቋማት የጠሩት ሰልፍ ነው፡፡ ይህ ሰልፍ በተዘዋዋሪ መንግስታችን የጠራው ሰልፍ መሆኑን ያወቅነው ቤት ለቤት እየቀሰቀሱ ያሉትን ቀበሌ ቀበሌ የሚጫወቱ ሴቶች ከማየታችን በፊት በኢቲቪ ዜና አንባቢው ጮክ ብሎ ሲናገር የሰማን ጊዜ ነው፡፡
እሁድ ነሀሴ 26 መንግስት፤ ተቀናቃኙ ሰማያዊ ፓርቲ ቀድሞ በጠራው ሰልፍ ላይ ሌላ ሰልፍ መጥራቱ ባስበው ባስበው አሁንም ባሰበው ምክንያቱ አልገለፅልህ ብሎኛል፡፡
ሰልፍን ደጋግሜ ሳንሰላስለው ሳንሰላስለው…. መንግስታችን ኢህአዴግ ይህንን ሰልፍ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀን ላይ ደርቦ ሲጠራ እንደው በደረቁ ሰልፍ ብሎ ከሚጠራ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች አንዳች ሆነ ግብዣ ቢያደርግ እና…
መሀል መስቀል አደባባይ ከሁለቱም ወገን የሚገኙ አመራሮች የሚሳተፉበት አይደል ሾው ነገር ወይም ደግሞ ድሮ ጊዜ እንደሚደረገው ሁለቱም ወገኖች አሉ የሚሏቸውን አዋቂዎቻቸውን አቁመው ርስ በርስ የሚሟገቱበት እና በህዝቡ ዘንድ የሀሳብ ብልጫ ለመያዝ ሙከራ የሚያደርጉበት የክርክር ውድድር ካልሆነ ካልሆነ ደግሞ የሆነ የቁንጅና ወድድር ነገር ቢያሳዩን ብዬ በማሰብ ላይ እገኛለሁ… ሸግዬ አሳብ አይደለም ትላላችሁ…!
የምር ግን ኢህአዴግ የጠራው ሰልፍ የምሩን ነው ማለት ነው…
እኔ የምለው የሀይማኖት ተቋማቱ መንግስት ይሄንን እንዲያደርጉ ሲያዛቸው ዝም ብለው እሺ ከሚሉት ሰብሰብ ብለው ፀልየው ከህመሙ እንዲፈወስ ቢያደርጉልን ምናለ… እውነቴን ነው ምላችሁ መንግስቴ ታሟል!
Abe Tokicha
w
Abe Tokicha
w
No comments:
Post a Comment