
የሟቾች ቁጥር አካራከሪ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ሞሞታቸው እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እየገለፁ ነው፡፡
ይህን ተከትሎ ግዚያዊ ፕሬዚዳንቱ አስቸኳይ አዋጅ ደንግገዋል፡፡
የግብፅ የፀጥታ ሃይሎች የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲ ደጋፊዎች የተቆጣጠሩት ስፍራ ለማስለቀቀ በወሰዱት እርምጃ ሰዎችን ሞሞታቸው ተከትሎ ግዚያዊ ፕሬዚዳንቱ አስቸኳይ አዋጅ ደንግገዋል፡፡
አዋጁ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ወር የሚዘልቅ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በእርምጃው የፀጥታ ሀይሎች 95 ሰዎች ሞሞታቸውን ሲገልፁ የሙስሊም ወንድማሞች ህብረት ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞሞታቸውን እየገለፀ ነው፡፡
ከሟቾቹ ውስጥ የታዋቂው ሙስሊም ወንድማሞችን እየመሩ የሚገኙት የሙሃመድ ኢል-በልታጊይየ17 አመት ሴት ልጅ ትገኛለች፡፡የስካይ ኒውስ ካሜራ ማን ሚክ ዲነም በአመፁ መገደሉ ታውቋል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር 95 ሰዎች እንደሞቱ ገልጿል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ በሃይል የተገደሉ ስለመኖሩ ያለው የለም ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱ መንግስት የፀጥታ ሃይሉ ካምፖችን ከሙርሲ ደጋፊዎች ለማስለቀቅ እየተወሰደ ባለው እርምጃ እንኳን ደስ ያላቹሀ ብሏል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
No comments:
Post a Comment