Friday, August 16, 2013

ድምፃዊ ኢዮብ መኮንን በጠና ታሟል “ኮማ” ውስጥ ነው


ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ሁሌም የሚያሽከረክራትን ብስክሌት ይዞ ከቤቱ የወጣው ድምጻዊ እዮብ መኮንን ወደቤቱ መመለስ እንደመሄድ ቀላል አልኾነለትም መኖሪያ ቤቱ መግቢያ ላይ ሲደርስ ‹‹አንድ እግሬ እንቢ አለኝ እስቲ ጫማ አውልቁልኝ›› አለና ተዝለፈለፈ ቤተሰቦቹ አፋፍሰው ወደ ሃያት ሆስፒታል ወሰዱት እዮብ ግን መናገር እየተሳነው ነበር፡፡ ሃያት ሆስፒታል ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ላካቸው እዮብ መናገርና ራሱን ማዘዝ እያቃተው ነበር፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያዎች እዮብን ተቀብለው ‹‹አዲስ ያስገባነው ነው›› ባሉት አየር መስጫ መሳይ ማሽን ላይ በማስተኛት እዮብን ለማንቃት ጥረታቸውን ጀመሩ ግን እስካሁን አልተቻላቸውም፡፡ እዮብ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ሪከቨሪ ውስጥ ራሱን እንደሳተ በማሽን መተንፈሱን ቀጥሏል፡፡ አተኛኘቱ እጅግ አንጀት ይበላል፡፡ በሆስፒታሉ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው በደቂቃዎች ክፍልፋይ የመንቃቱን ዜና ይጠባበቃል፡፡ በአንዷ ደቂቃ ፈጣሪ በድንገት እንዲያነቃው ሁላችንም እንፀልይለት፡፡

No comments:

Post a Comment