ከሓየሎም መንደር ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል by Abreha Desta
በትግራይ ሽረ አከባቢ ነው። ስለ ሽረ ሲነሳ ስለ ሓየሎም ነው የማብሰለስለው። ስለ ሓየሎም ሳስብ ጀግንነት ይሰማኛል። በህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ የሽሬ አርሶአደሮች ነበሩ። በአሁኑ ግዜ ደግሞ ልማት ከተነፈጉ የትግራይ አከባቢዎች ግንባር ቀደም ናቸው።
የህወሓት አመራር ያንገሸገሻቸው የሽረ ተወላጆች የሆኑ የድሮ የህወሓት ታጋዮች ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ። የታጋዮቹ መነሳሳት የህወሓት ባለስልጣናትን እጅግ አስግታቸዋል።
ከወደ ሽረ የሰማሁት ነገር ልጨምርና ላብቃ።
የሽረ ተወላጆች የልማት ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የአከባቢው አስተዳዳሪዎችም ሁሌ እንደሚያደርጉት ህዝብ ሰብሰበው
"እነኚህ ሆስፒታል፣ ትምህርትቤትና መንገድ እንዲሰራ የሚጠይቁ ሰዎች ጠላቶች ናቸው፣ ተቃዋሚዎች ናቸው፣ ዓረና ናቸው። ስለዚህ እንዳት ሸወዱ፣ እነሱን እንዳትደግፉ።" እያሉ ያስጠነቅቃሉ።
ከአከባቢው ተወላጆች አንድ ተነስቶ "እነኚህ ተቃዋሚዎች፣ ጠላቶች፣ ዓረናዎች ሆስፒታል፣ ትምህርትቤትና መንገድ እንዲሰራ የሚፈልጉ ከሆኑማ ከናንተ በጣም ይሻላሉ። ስለዚህ እነሱ ይሻሉናል።" ሲሉ ተሰብሳቢው በሳቅ ፈረሰ።
(ከጓደኛዬ ያገኘሁት መረጃ ነው)።
አዎ! ሓየሎምን አስታውሳለሁ፣ አከብራለሁ።
ሓየሎም ፈንቅል።
No comments:
Post a Comment