አዲሱ አስተምህሮተ ክርስትና
በ1997 ምርጫ ሰሞን የሃይማኖት ሰዎች በቤተመንግስቱ አካባቢ ጥሪ ተደርጎላቸው ተሰብስበው እንደነበር ትዝ ይለኛል። ያንጊዜ ኦርቶዶክሳዊቷን ቤተክርስቲያን ወክለው ከተገኙት ውስጥ አንድ ሰው ተነስተው መለስ የሚባል ሰው አገር አንደሚገዛ በትግራይ የቀየ ንግርት አለ ብለው ተናግረው ነበር። ይህንን ተከትሎ አንድ የካቶሊክ ተወካይ ‘ አይ እነዲህ ያለነገር ልክ አይደለም ቤተመንግስት እጣን እጣን ቤተክርስቲያንም ፐለቲካ ፐለቲካ ስትሸት ደግ አይደለም እነዳሉ አስታውሳለሁ።
እኝህ ሰው የሃገሪቱንም ህገመንግስት ለመጣስ ምንም የሞራልም ይሁን የአፍ ዳገት አልገጠማቸውም። በንግግራቸው ኢትዮጵያ የማታወቃቸው ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ አሉ’ ብለዋል። መለኪያቸውም እነዚህ ኢትዮጵያውያን አቶ መለስን አለማድነቃቸው ነው። ለእሳቸው ኢትዮጵያ የምታውቃቸው ኢትዮጵያውያን አቶ መለስን የሚወዱ እና የሚያከብሩ ብቻ ናቸው እንጂ በህገመንግስቱ ስለዜግነት የተደነገገው ለእሳቸውም ሆነ ይን ንግግር ሲያደምጡ በጭብጨባ ላጀቡት የስብሰባው አድምተኞች ፋይዳቢስ ነበር። ‘’ በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፡ ይገባል ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።’’ (ዮሃንስ 10፡-9) የሚለውን የክርስቶስ ቃል በሚመስል ንጽረት የኢትዮጵያዊነት ዜግነትን እና በዜግነትም መታወቅን ልናገኝ የምንችለው በአቶ መለስ ስናምን እና አሳቸውን ስንወድስ ብቻ አነደሆነ ነግረውናል። በኢትየጵያዊነት አንድ የምንሆነውም እንደዛው። ‘መነኩሴው’ ይህን ሁሉ ሲሉ ሌላም የህገመንግስት አንቀጽ እንደጣሱ ግልጽ ነው። ምንም እንኩዋን ፐለቲከኛ እንዳልሆኑ አስቀድመው ቢናዘዙም ቤተክርስቲያንን ወክለው እና ጥቁር ሃይማኖታዊ ልብሳቸውን ለብሰው ባቀረቡት ንግግራቸው ከሁለት የፖለቲካ ጎራወች አንዱን በመደገፍና ሌላውን በማንኳሰስ ሌልኛውን ህገመንግስት- ሃይማኖት በመንግስት/ በፐለቲካው ውስጥ ጣልቃ አይገባም የሚለውን ጥሰዋል።
አንዳንድ ሰወች ግለሰባዊ አምልኮ /personality cult/ እየተፈጸመ ነው የሚሉትን ነገር ተግባራዊ ማስረጃ በሚሆን መልኩ ‘መነኩሴው’ ፈጽመዋል። ምእመኖቻቸውም ይህንንው አብረዋቸው አከናውነዋል። ማን ያውቃል ትላንት አጼ ሐይለስላሴን የሚያመልኩ ሰወች እንደተፈጠሩ አሁን ደግመ አቶ መለስን የሚያመልኩ ሰወች ቢደገሙስ? መነኩሴው በእሳቸው ስም ገዳም ቢያቋቁሙልንስ ምን ይላቸዋል?
እኒህ መነኩሴ ተሳዳቢም ናቸው። በንግግራቸው ‘’ ዲያሰፖራ ሳይሆን ኤልፎራ ናቸው’’ ብለዋል። ይህ ንግግር ሲፈታ ሁለት አንድምታ ሊኖረው ይችል ይሆናል። የቤተክህነት ሰው ስለሆኑ ቅኔ ተምረው የለ? የመጀመሪያው እንዲህ ወደ አውሮፓ ስደታቸውን ያቀኑትን ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰወች ዲያሰፖራ ብለው እየጠሩ የስደት እግራቸው ወደ አረብ ሃገራት ያቀናውን ሰዎች ደግሞ ‘ኤልፎራ’ ሲሉ ይደመጣሉ።ሁለተኞቹን በመናቅ ድምጸት። እኝህ ‘መነኩሴ’ አንድም እንዲህ ማድረጋቸው እና ነገሩን እና ስሙን አገላብጠው መጠቀማቸው ሲሆን አንድም በአዲስ አበባ ንብረትነቱ የሼክ አላሙዲን የሆነው ኤልፎራ የዶሮ እርባታ ስም ስለሆነ አቶ መለስን የማይደግፉ ሰወች ዶሮዎች ናቸው ማለታቸው ይሆናል።
እንግዲህ ቤተክህነት ይህን መሰል ጉድ ይዛ፣ ህዝቧን አንድ ባደረገው ክርስቶስ አንድ ከመሆን ይልቅ በአቶ መለስ አንድ የሆኑ መሪዎች መርተዋት፣ እንዴት ቤተክርስቲያን ትሆነው ይሆን? ለእርሷ ‘’ እኔ መንገድ እና አውነት ህይወትም ነኝ’’ ከሚለው ጌታ ይልቅ ሌላ አውነት ኑሯት እና ይህን የማይቀበሉትን ክርስቲያኖች አግልላና አውግዛ ወዴት ታመራ ይሆን? ግን ግን ክርስቶስ የሞተው እና ለራሱ ቤተክርስቲያንን የዋጀው ‘አውነት በሆኑት’ በአቶ መለስ የሚያምኑትን ብቻ ለመሰብሰብ ይሆን እንዴ?
እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ‘’እውነት’ እና የአንድነት መሰረቷ አቶ መለስ ከሆኑ የእሳቸውን አመራር፣ አመለካከት እና ፖሊሲዎች ያልደገፉ ወይም የተቃወሙ ክርስቲያኖች ክርስትናቸው ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ገባ ማለት ነው። እኝህ መነኩሴ የብዙ ህዝቦችን ዜግነት እና ሃይማኖታዊ እምነት የሰረዘና ህዝቦች ኢትዮጵያዊ ለመሆንም ሆነ ክርስቲያን ለመሆን እሳቸው የሰበኩትን ‘እውነት’ ለመቀበል በ መለሲዝም መጠመቅ እንዳለባቸው አውጀዋል። ይህ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ንግግር እንዲያቀርቡ በኦፊሴል የላከቻቸው የሃይማኖት አባት የተናገሩትን በአፊሴል እስካላስተባበለች ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ መቀየሩን ማወጁዋን ያረጋግጣል።
ይህ ከሆነ ደግሞ መጻህፍ ቅዱሳዊው አስተምሮ ቀርቶ መደበኛ የሆነው የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሰብ እንኩዋን የሚፈቅደውን ነጻ አስተሳሰብ እንኩዋን በመቃወም ቤተክርስቲያኒቱን አንባገነን የደርጋታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጥንታዊነቷ እና በምስራቅ አፍሪካ ክርስትናን ጠብቃ መቆየቷ የሚወደስ ምግባሯ ቢሆንም ድሮ ለነገስታቱ አሁንም ደግሞ ላሉት መሪዎች አንፋሽ አጎንባሽ መሆኗ አሳሳቢ ነው።
ግን እነዲህ ያለውን ‘’ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች’’ በሚባል ሁኔታ ሰወች በተቁዋማት ላይ የሚፈጽ ሙትን ጥፋት ቤተክርስቲያኒቱ ልታርም ብትነሳ መንግስት በእርግጥ ቅር አይለውም ይሆን?
An Ethiopian Priest speaks at the memorial service of the late PM Melese Zenawi has declared that Mr. Melese is the truth like that of Christ the Lord.
This comment has been removed by the author.
ReplyDelete